Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 21:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ዳዊትም ለካህኑ መልሶ “ከብላቴኖቼ ጋር ወደ ተልእኮ በምሄድበት ጊዜ ሁሉ ከሴቶች እንርቃለን፤ ተራ ተልእኮ እንኳ በምናደርግበት ጊዜ ብላቴኖቼ ንጽሕናቸውን ይጠብቃሉ። ዛሬማ ምንኛ የበለጠ ቅዱሳን መሆን ይገባቸዋል?”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ዳዊትም “እንደተለመደው ሁሉ ከወጣሁ ጊዜ ጀምሮ ሴቶች ከእኛ ተጠብቀዋል፤ ባልተቀደሰ ተልእኮ ውስጥ እንኳ የሰዎቹ ዕቃዎች የተቀደሱ ናቸው፤ ታዲያ ዛሬማ እንዴት!” ሲል ለካህኑ መለሰ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ዳዊትም “እንደተለመደው ሁሉ ከወጣሁ ጊዜ ጀምሮ ሴቶች ከእኛ ተጠብቀዋል፤ በተራ ተልእኮ ውስጥ እንኳ የሰዎቹ ዕቃዎች የተቀደሱ ናቸው፤ ዛሬማ ምንኛ የበለጠ ቅዱሳን መሆን ይገባቸዋል?” ሲል መለሰ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ዳዊ​ትም ለካ​ህኑ መልሶ፥ “ከሴ​ቶች ተለ​ይ​ተን ወደ መን​ገድ ከወ​ጣን ዛሬ ሦስ​ተኛ ቀና​ችን ነው። እኔም ብላ​ቴ​ኖ​ቼም ንጹ​ሓን ነን። ነገር ግን ዛሬ ሰው​ነቴ ንጽ​ሕት ስለ ሆነች ነው እንጂ ይህች መን​ገድ የነ​ጻች አይ​ደ​ለ​ችም” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ዳዊትም ለካህኑ መልሶ፦ በእውነት ከወጣን ጀምረን እኛ ሰውነታችንን ከሴቶች ሦስት ቀን ጠብቀናል፥ የብላቴኖችም ዕቃ የተቀደሰች ናት፥ ስለዚህ ዛሬ እቃቸው የተቀደሰች በመሆንዋ እንጀራው እንደሚበላ እንጀራ ይሆናል አለው።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 21:5
10 交叉引用  

ከዚህ በኋላ ሙሴ ከተራራው ወርዶ ሕዝቡ ልብሱን አጥቦ እንዲቀደስ አደረገ፤


ሙሴም ሰዎቹን “ለተነገወዲያው ዕለት ተዘጋጁ፤ እስከዚያም ቀን ድረስ ወደ ሴት አትቅረቡ” አላቸው።


ጠረጴዛውም በታቦቱ ፊት ለፊት ይቀመጥ፤ ለእኔ የሚቀርበው የተቀደሰ ኅብስት ዘወትር በጠረጴዛው ላይ መኖር አለበት።


ይህም የእስራኤል ሕዝብ ዘወትር ሊፈጽሙት የሚገባ የቃል ኪዳን ሥርዓት ነው። ኅብስቱ የአሮንና የልጅ ልጆቹ ድርሻ ይሆናል፤ እነርሱም በተቀደሰ ቦታ ይብሉት፤ እርሱ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል ቅዱስ መሥዋዕት ሆኖ ከቀረበ በኋላ ለካህናቱ የተለየ ቋሚ ድርሻ ይሆናል።”


በእግዚአብሔር ፊት ካለው እርሾ ያልነካው ቂጣ ከሚቀመጥበትም መሶብ አንድ ኅብስት ወሰደ፤ እንዲሁም በዘይት የታሸ አንድ ኅብስትና አንድ ስስ ቂጣ ወስዶ በስቡና በቀኝ እግሩ ላይ አኖረው፤


ጌታም ሐናንያን እንዲህ አለው፦ “እርሱ ስሜን ለአረማውያን፥ ለነገሥታትና ለእስራኤል ሰዎች የሚያሳውቅ፥ የእኔ ምርጥ መሣሪያ ስለ ሆነ ወደ እርሱ ሂድ፤


በጸሎት ለመትጋት ሁለታችሁም ተስማምታችሁ ለተወሰነ ጊዜ ካልሆነ በቀር በመለያየት አንዱ የሌላውን የጋብቻ መብት አይከልክል። በዚህም ምክንያት ራሳችሁን መቈጣጠር አቅቶአችሁ ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ እንደገና አብራችሁ ሁኑ።


የእግዚአብሔር ፈቃድ ከሆነ እናንተ ክፉ ነገርን በማድረግ መከራ ከምትቀበሉ መልካም ነገርን በማድረግ መከራ ብትቀበሉ ይሻላል።


跟着我们:

广告


广告