Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 18:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 የለበሰውንም ካባ አውልቆ ለዳዊት ሰጠው፤ እንዲሁም የጦር ልብሱን፥ ሰይፉን፥ ቀስቱንና መታጠቂያውን ጭምር ሰጠው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ዮናታን የለበሰውን ካባ አውልቆ ከነጦር ልብሱ፣ በተጨማሪም ሰይፉን፣ ቀስቱንና መታጠቂያውን ሰጠው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ዮናታን የለበሰውን ካባ አውልቆ ከነጦር ልብሱ፥ በተጨማሪም ሰይፉን፥ ቀስቱንና መታጠቂያውን ሰጠው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ዮና​ታ​ንም የለ​በ​ሰ​ውን ካባ አው​ልቆ እር​ሱ​ንና ልብ​ሱን፥ ሰይ​ፉ​ንም፥ ቀስ​ቱ​ንም፥ ዝና​ሩ​ንም ለዳ​ዊት ሸለ​መው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ዮናታንም የለበሰውን ካባ አውልቆ እርሱንና ልብሱን ሰይፉንም ቀስቱንም መታጠቂያውንም ለዳዊት ሸለመው።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 18:4
10 交叉引用  

ንጉሡ የሥልጣኑ ምልክት ያለበትን የማኅተም ቀለበት ከጣቱ አውልቆ በዮሴፍ ጣት ላይ አደረገው፤ ከጥሩ ሐር የተሠራ ልብስ አለበሰው፤ በአንገቱም የወርቅ ሐብል አደረገለት።


የዮናታን ቀስት ሳይገድል የማይመለስ፥ የሳኦልም ሰይፍ ጠላትን የሚቈራርጥ ኀያላንን መትቶ የሚሰብር፥ ጠላትን የሚገድል ነበር።


እኔ በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ ሁለንተናዬም በአምላኬ ሐሴትን ያደርጋል፤ የአበባ አክሊል በራሱ ላይ እንደሚያደርግ ሙሽራ፥ በጌጣጌጥም እንዳሸበረቀች ሙሽሪት አድርጎ፥ የመዳንን ልብስ አልብሶኛል፤ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛል።


አባቱ ግን አገልጋዮቹን ጠርቶ እንዲህ አለ፦ ‘ቶሎ ብላችሁ ከሁሉ የበለጠውን ልብስ አምጡና አልብሱት! በጣቱ ቀለበት፥ በእግሩም ጫማ አድርጉለት!


እኛ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ጽድቅ ተካፋዮች እንድንሆን እግዚአብሔር ኃጢአት የሌለበትን ክርስቶስን የእኛን ኃጢአት እንዲሸከም አደረገው።


ሳኦልም የገዛ ራሱን የጦር ልብስ ለዳዊት አለበሰው፤ ከነሐስ የተሠራውን የራስ ቊር በዳዊት ራስ ላይ ደፍቶ ጥሩርም አለበሰው፤


ሳኦል በትእዛዝ በሚያዘምትበት ቦታ ሁሉ የዳዊት ተልእኮ የተሳካ ሆነ፤ ስለዚህም ሳኦል በጦር ሠራዊቱ ውስጥ የመኰንንነት ማዕርግ እንዲኖረው አደረገ፤ ይህም የሳኦልን የጦር መኰንኖችና ወታደሮችን ሁሉ አስደሰተ።


跟着我们:

广告


广告