Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 17:53 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

53 እስራኤላውያንም እነርሱን አሳደው ከተመለሱ በኋላ ፍልስጥኤማውያን የነበሩበትን ሰፈር ዘረፉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

53 እስራኤላውያን ፍልስጥኤማውያንን ከማሳደድ ተመለሱ፤ ሰፈራቸውንም በዘበዙ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

53 እስራኤላውያን ፍልስጥኤማውያንን አሳደው ተመለሱ፤ ሰፈራቸውንም በዘበዙ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

53 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ከማ​ሳ​ደድ ተመ​ል​ሰው ሰፈ​ራ​ቸ​ውን በዘ​በዙ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

53 የእስራኤልም ልጆች ፍልስጥኤማውያንን ከማሳደድ ተመልሰው ሰፈራችውን በዘበዙ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 17:53
7 交叉引用  

ይህ ሰው ግን ባለበት ጸንቶ በመቆም እጁ ዝሎ በሰይፉ ላይ እስኪጣበቅ ድረስ ፍልስጥኤማውያንን ወጋ፤ በዚያን ቀን እግዚአብሔር ታላቅ ድልን አደረገ፤ ጦርነቱም ከቆመ በኋላ እስራኤላውያን አልዓዛር ወደነበረበት ስፍራ ተመልሰው ከሞቱት ፍልስጥኤማውያን ብዙ የጦር ልብስ ማረኩ።


ነገር ግን እናንተን ግጠው የበሉአችሁ ሁሉ እነርሱም በፈንታቸው ተግጠው ይበላሉ፤ ጠላቶቻችሁ ሁሉ ተማርከው ይወሰዳሉ፤ ሲዘርፉአችሁ የነበሩት ሁሉ ይዘረፋሉ። የቀሙአችሁ ሁሉ እነርሱም በተራቸው እንዲቀሙ አደርጋለሁ።


መቅሠፍት በመቅሠፍት ላይ ይደራረባል፤ አገሪቱ በሙሉ ፈራርሳ ጠፍ ሆናለች፤ ድንኳኖቻችን በድንገት ወደሙ፤ መጋረጃዎቻቸውም በቅጽበት ተቀደዱ።


ከዚህ በኋላ የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎች ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እየፎከሩ እነርሱን በመከተል እስከ ጋትና እስከ ዔቅሮን የቅጽር በሮች ድረስ አሳደዱአቸው፤ የፍልስጥኤማውያን ሬሳ እስከ ጋትና እስከ ዔቅሮን ድረስ ወደ ሻዕራይም በሚያደርሰው መንገድ ሁሉ ወደቀ።


ዳዊት የጎልያድን ራስ ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው፤ የጎልያድን የጦር መሣሪያዎች ግን በራሱ ድንኳን አስቀመጠ።


እርሱ ለሕይወቱ ሳይሳሳ በመጋፈጥ ጎልያድን ገደለ፤ እግዚአብሔርም ለእስራኤል ታላቅ ድልን አቀዳጀ፤ አንተም ይህን ባየህ ጊዜ ደስ ብሎህ ነበር፤ ታዲያ አሁን አንተ በንጹሕ ሰው ላይ በደል ለመሥራት ስለምን ታስባለህ? ምክንያት በሌለውስ ነገር ዳዊትን ለመግደል ስለምን ፈለግኽ?”


跟着我们:

广告


广告