Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 11:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ናዖስም “ከእናንተ ጋር የውል ስምምነት ማድረግ የምችልበት አንድ ዐይነት ግዴታ አለ፤ ይኸውም የእያንዳንዱን ሰው ቀኝ ዐይን በማውጣት በእስራኤላውያን ላይ አሳፋሪ ውርደት አመጣለሁ” ሲል መለሰላቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 አሞናዊው ናዖስ፣ “ከእናንተ ጋራ ቃል ኪዳን የማደርገው የእያንዳንዳችሁን ቀኝ ዐይን አውጥቼ እስራኤልን ሁሉ ካዋረድሁ በኋላ ብቻ ነው” ሲል መለሰ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 አሞናዊው ናዖስ ግን፥ “ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳን የማደርገው የእያንዳንዳችሁን ቀኝ ዐይን አውጥቼ እስራኤልን ሁሉ ካዋረድሁ በኋላ ብቻ ነው” ሲል መለሰ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 አሞ​ና​ዊው ናዖ​ስም፦“ ቀኝ ዐይ​ና​ች​ሁን ብታ​ወጡ ከእ​ና​ንተ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ላይ ስድ​ብን አደ​ር​ጋ​ለሁ” አላ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 አሞናዊውም ናዖስ፦ ቀኝ ዓይናችሁን ሁሉ በማውጣት ቃል ኪዳን አደርግላችኋለሁ፥ በእስራኤልም ሁሉ ላይ ስድብ አደረጋለሁ አላቸው።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 11:2
11 交叉引用  

“እኅታችንን ያልተገረዘ ሰው እንዲያገባት አንፈቅድም፤ ይህ ለእኛ ታላቅ ውርደት ነው፤


ሕዝቅያስ የሚላችሁን አታዳምጡ፤ የአሦር ንጉሠ ነገሥት ከከተማችሁ ወጥታችሁ እጃችሁን እንድትሰጡ አዞአችኋል፤ ይህን ብታደርጉ ሁላችሁም እያንዳንዳችሁ የወይን ተክሎቻችሁን ዘለላና የበለስ ዛፎቻችሁን ፍሬ ትበላላችሁ፤ ከጒድጓዶቻችሁም ውሃ ትጠጣላችሁ፤


በጐረቤቶቻችን የምንነቀፍ አደረግኸን፤ በዙሪያችን ላሉትም መዘባበቻና መሳለቂያ አደረግኸን።


እኔ የቀድሞ አባቶችህ የአብርሃም፥ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ ነኝ፤” በዚህ ጊዜ ሙሴ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት ማየት ስለ ፈራ ፊቱን ሸፈነ።


ደግ ሰው ለቤቱ እንስሳት ይራራል፤ የክፉ ሰው ርኅራኄ ግን ጭካኔ ነው።


ከዚህም ሁሉ በኋላ የሴዴቅያስን ዐይኖች አወጣ፤ ወደ ባቢሎንም ለመውሰድ በነሐስ ሰንሰለት አሰረው።


ለም ወደሆነችው ምድር እንዳላመጣኸን ወይም የእርሻና የወይን ተክል ቦታ እንዳላወረስከን የተረጋገጠ ነው፤ አሁን ደግሞ ልታታልለን ትፈልጋለህ፤ እንግዲህስ ወደ አንተ አንመጣም!”


ፍልስጥኤማውያንም ከማረኩት በኋላ ሁለቱን ዐይኖቹን አወጡ፤ ወደ ጋዛም ወስደው በነሐስ ሰንሰለት በማሰር በታሰረበት ቤት እህል እንዲፈጭ አደረጉት፤


የያቤሽም ሰዎች አሞናውያንን “ነገ እጃችንን ለእናንተ እንሰጣለን እናንተም በእኛ ላይ የምትፈልጉትን አድርጉ” አሉአቸው።


እናንተ ግን እግዚአብሔር አምላካችሁ ንጉሣችሁ ሆኖ ሳለ የአሞን ንጉሥ ናዖስ በእናንተ ላይ መነሣቱን ባያችሁ ጊዜ ‘አይሆንም ንጉሥ አንግሥልን’ አላችሁ።


ዳዊትም በአጠገቡ የቆሙትን ሰዎች “ይህን ፍልስጥኤማዊ ገድሎ እስራኤልን ከዚህ አሳፋሪ ውርደት ለሚያድን ሰው ምን ይደረግለታል? ኧረ ለመሆኑ የሕያው እግዚአብሔርን ሠራዊት የሚፈታተን ይህ ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ ማን ነው?” ሲል ጠየቀ።


跟着我们:

广告


广告