Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 10:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በዚያም የሚኖር አንድ ሰው “የእነዚህስ የሌሎቹ ነቢያት ሁኔታ እንዴት ነው? አባቶቻቸውስ እነማን ናቸው?” ሲል ጠየቀ፤ “ሳኦልም ደግሞ ከነቢያት ወገን ነውን?” የሚል የምሳሌ አነጋገር የመነጨውም ከዚህ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 በዚያ ነዋሪ የሆነ አንድ ሰው፣ “የእነርሱስ አባት ማን ነው?” ብሎ መለሰ። ስለዚህ፣ “ሳኦልም ከነቢያት ወገን ነውን?” የሚል ምሳሌያዊ አነጋገር ሆነ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በዚያ ነዋሪ የሆነ አንድ ሰው፥ “አባታቸውስ ማን ነው?” ብሎ መለሰ። ስለዚህ፥ “ሳኦልም ከነቢያት ወገን ነውን?” የሚል ምሳሌያዊ አነጋገር ሆነ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ከዚ​ያም ስፍራ ያለ አንድ ሰው፥ “አባ​ቱስ ማን ነው?” ብሎ መለሰ። ስለ​ዚ​ህም “ሳኦል ደግሞ ከነ​ቢ​ያት ወገን ነውን?” የሚል ምሳሌ ሆነ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ከዚያም ስፍራ ያለ አንድ ሰው፦ አባታቸውስ ማን ነው? ብሎ መለሰ። ስለዚህም፦ ሳኦል ደግሞ ከነቢያት ወገን ነውን? የሚል ምሳሌ ሆነ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 10:12
7 交叉引用  

“ልጆችሽ ሁሉ ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ፤ የልጆችሽም ሰላም የተሟላ ይሆናል።


በነቢያት መጻሕፍት ‘ሰዎች ሁሉ ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ’ ተብሎ ተጽፎአል፤ ስለዚህ ከአብ ሰምቶ የተማረ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል።


ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “የእኔ ትምህርት ከላከኝ ከአብ የተገኘ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም።


መልካም ስጦታና ፍጹም በረከት ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፤ ይህም የሚመጣው እንደ ጥላ መዘዋወር ወይም መለዋወጥ ከሌለበት ከብርሃን አባት ከእግዚአብሔር ነው።


ሳኦልም ትንቢት መናገሩን ከፈጸመ በኋላ በኮረብታው ላይ ወደሚገኘው መሠዊያ ወጣ።


ወደዚያም በማምራት ላይ ሳለ የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱም ላይ ወረደበት፤ እስከ ናዮት በሚያደርሰው መንገድ ሁሉ ትንቢት ይናገር ነበር፤


ወደ ሳሙኤልም ፊት ሲቀርብ ልብሱን አውልቆ ትንቢት እየተናገረ፤ ቀኑንም ሌሊቱንም ሁሉ ራቁቱን በዚያው ተጋድሞ ዋለ፤ “ሳኦልም ከነቢያት እንደ አንዱ ሆኖ ተቈጠርን?” የሚለው የምሳሌ አነጋገር የመነጨው ከዚህ የተነሣ ነው።


跟着我们:

广告


广告