Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 8:54 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

54 ሰሎሞን ጸሎቱን ከፈጸመ በኋላ እጆቹን እንደ ዘረጋ ተንበርክኮ ከነበረበት መሠዊያ ፊት ተነሥቶ ቆመ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

54 ሰሎሞንም ይህን ሁሉ ጸሎትና ልመና ለእግዚአብሔር አቅርቦ ከፈጸመ በኋላ፣ እጆቹን ወደ ሰማይ በመዘርጋት፣ በጕልበቱ ተንበርክኮ ከነበረበት ከእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት ተነሣ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

54 ሰሎሞን ጸሎቱን ከፈጸመ በኋላ እጆቹን እንደ ዘረጋ ተንበርክኮ ከነበረበት መሠዊያ ፊት ተነሥቶ ቆመ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

54 ሰሎ​ሞ​ንም ይህ​ችን ጸሎ​ትና ልመና ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸልዮ በፈ​ጸመ ጊዜ፥ በጕ​ል​በቱ ተን​በ​ር​ክኮ፥ እጁ​ንም ወደ ሰማይ ዘር​ግቶ ነበ​ርና ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ፊት ከሰ​ገ​ደ​በት ተነሣ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

54 ሰሎሞንም ይህችን ጸሎትና ልመና ሁሉ ለእግዚአብሔር ጸልዮ በፈጸመ ጊዜ፥ በጕልበቱ ተንበርክኮ እጁንም ወደ ሰማይ ዘርግቶ ነበርና ከእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት ተነሣ።

参见章节 复制




1 ነገሥት 8:54
9 交叉引用  

ከዚህ በኋላ ሰሎሞን በሕዝቡ ፊት ተነሥቶ በመሠዊያው ፊት ለፊት ቆመ፤ እጆቹንም ወደ ሰማይ ዘረጋ፤


ንጉሥ ሰሎሞን ጸሎቱን እንደ ፈጸመ ወዲያውኑ እሳት ከሰማይ ወርዶ የሚቃጠለውንና ሌላውን መሥዋዕት በላ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ቤተ መቅደሱን ሞላው፤


ኑ፤ ዝቅ ብለን እንስገድ! በፈጣሪያችን በእግዚአብሔር ፊት እንንበርከክ!


አንድ ቀን ኢየሱስ በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፤ ጸሎቱንም ባበቃ ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፥ “ጌታ ሆይ! ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን ጸሎት እንዳስተማራቸው፥ አንተም እኛን መጸለይ አስተምረን!” አለው።


41 ከዚህ በኋላ የድንጋይ ውርወራ ያኽል ከእነርሱ ራቅ ብሎ ሄደ፤ ተንበርክኮም እንዲህ ሲል ጸለየ፦


ከጸሎቱ ተነሥቶ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መጣ፤ ከሐዘን ብዛት የተነሣ ተኝተው አገኛቸውና እንዲህ አላቸው፤


ከዚህ በኋላ ጳውሎስ ከሁሉም ጋር ተንበርክኮ ጸለየ።


እዚያ የምንቈይበት ጊዜ ሲያልቅ ተለይተናቸው ጒዞአችንን ቀጠልን፤ ሁሉም ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር ሆነው እስከ ከተማው ውጪ ድረስ ሸኙን፤ በባሕሩም ዳር ተንበርክከን ከጸለይን በኋላ ተሰነባበትን።


跟着我们:

广告


广告