1 ነገሥት 7:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 ሰሎሞንም ሑራም የተባለውን ሰው ከጢሮስ ከተማ አስጠራ፤ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም13 ንጉሥ ሰሎሞንም መልእክተኛ ልኮ ኪራም የተባለውን ሰው ከጢሮስ አስመጣ፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 ሰሎሞንም ሑራም የተባለውን ሰው ከጢሮስ ከተማ አስጠራ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 ንጉሡም ሰሎሞን ልኮ ኪራምን ከጢሮስ አስመጣ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 ንጉሡም ሰሎሞን ልኮ ኪራምን ከጢሮስ አስመጣ። 参见章节 |
ሑራም በተጨማሪ ምንቸቶችን፥ መጫሪያዎችንና ማንቈርቈሪያዎችንም ሠራ፤ በዚህ ሁኔታም ሑራም ለንጉሥ ሰሎሞን እንዲሠራለት ቃል በገባለት መሠረት ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት የሚውለውን ዕቃ ሁሉ ሠርቶ ፈጸመ፤ የሠራቸውም ዕቃዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው፦ ሁለት ምሰሶዎች፥ በምሰሶዎቹ ጫፍ ላይ የሚገኙት የሳሕን ቅርጽ ያላቸው ሁለት ጒልላቶች፥ ሁለቱን ጉልላቶች ለማስጌጥ በእያንዳንዱ ጒልላት ላይ የሚገኙት በመርበብ አምሳል የተቀረጹት ሁለት ሰንሰለቶች፥ ጉልላቶቹን ለማስጌጥ በእያንዳንዱ ጒልላት ላይ በሁለት ዙር የተቀረጹ ከነሐስ የተሠሩ አራት መቶ የሮማን ፍሬ ምስሎች፥ ዐሥሩ ባለመንኰራኲር የዕቃ ማስቀመጫዎች፥ ዐሥሩ የመታጠቢያ ገንዳዎች፥ ትልቁ ገንዳ፥ በርሜሉን ደግፈው የያዙት የዐሥራ ሁለቱ በሬዎች ቅርጾች፥ ምንቸቶች፥ መጫሪያዎች፥ ሜንጦዎችና ሌሎችም እነዚህን የመሳሰሉ ዕቃዎች በእጅ ጥበብ ሠራ። ታዋቂ የሆነው ሑራም በንጉሥ ሰሎሞን ትእዛዝ መሠረት ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት ይውሉ ዘንድ እነዚህን ዕቃዎች ሁሉ የሠራው ከተወለወለ ነሐስ ነበር።