Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 20:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ሶርያውያንና እስራኤላውያን ፊት ለፊት ተፋጠው በየጦር ሰፈራቸው እስከ ሰባት ቀን ቈዩ፤ በሰባተኛውም ቀን ጦርነት ጀምረው በዚያኑ ቀን እስራኤላውያን አንድ መቶ ሺህ የሶርያውያንን እግረኛ ጦር ወታደሮችን ገደሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 በየሰፈሩበትም ቦታ ሰባት ቀን ከተፋጠጡ በኋላ በሰባተኛው ቀን ጦርነት ገጠሙ። እስራኤላውያንም በአንዲት ጀምበር ከሶርያውያን ሰራዊት መቶ ሺሕ እግረኛ ገደሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ሶርያውያንና እስራኤላውያን ፊት ለፊት ተፋጠው በየጦር ሰፈራቸው እስከ ሰባት ቀን ቆዩ፤ በሰባተኛውም ቀን ጦርነት ጀምረው በዚያኑ ቀን እስራኤላውያን አንድ መቶ ሺህ የሶርያውያንን እግረኛ ጦር ወታደሮችን ገደሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 “አክ​ዓብ በፊቴ እንደ ደነ​ገጠ አየ​ህን? በፊቴ በልጁ ዘመን በቤቱ ላይ ክፉ ነገር አመ​ጣ​ለሁ እንጂ በእ​ርሱ ዘመን ክፉ ነገር አላ​መ​ጣም።”

参见章节 复制




1 ነገሥት 20:29
13 交叉引用  

ይስሐቅ የባቱኤልን ልጅ ርብቃን ሲያገባ አርባ ዓመት ሆኖት ነበር፤ የርብቃ አባት ባቱኤልና ወንድምዋ ላባ በመስጴጦምያ የሚኖሩ ሶርያውያን ነበሩ፤


እስራኤላውያን ሶርያውያንን መልሰው አሳደዱአቸው፤ ዳዊትና ሠራዊቱ ሰባት መቶ የሶርያውያንን ሠረገለኞችንና አርባ ሺህ ፈረሰኞችን ገደሉ፤ እንዲሁም የጠላት ሠራዊት አለቃ የነበረውን ሾባክን መተው አቊስለውት ስለ ነበር እዚያው በጦር ሜዳው ላይ ሞተ።


አንድ የእግዚአብሔር ነቢይ ወደ ንጉሥ አክዓብ ቀርቦ “እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ ‘ሶርያውያን፦ እግዚአብሔር የኮረብቶች አምላክ እንጂ የሜዳዎች አምላክ አይደለም ብለዋል፤ ከዚህም የተነሣ እኔ እጅግ ብዙ በሆነው ሠራዊታቸው ላይ ድልን አቀዳጅሃለሁ፤ አንተና ሕዝብህም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ’ ” አለው።


ከሞት የተረፉትም ሶርያውያን ሸሽተው ወደ አፌቅ ከተማ ገቡ፤ በዚያም ቊጥራቸው ኻያ ሰባት ሺህ በሚሆኑት ወታደሮች ላይ የከተማው ቅጽር ተንዶባቸው አለቁ። ቤንሀዳድም አምልጦ ወደ ከተማይቱ በመግባት ከአንድ ቤት በስተ ኋላ በኩል ባለው ክፍል ውስጥ ተደበቀ።


ኤልሳዕ “የምሥራቁን መስኮት ክፈት” አለ፤ ንጉሡም ከፈተው፤ ኤልሳዕም “ፍላጻውን አስፈንጥር!” አለው፤ ንጉሡም ፍላጻውን እንዳስፈነጠረ ወዲያውኑ ኤልሳዕ፥ “ፍላጻ ነህ፤ በአንተም አማካይነት እግዚአብሔር ሶርያውያንን ድል ያደርጋል፤ ሶርያውያንን ድል እስክትነሣቸው ድረስ በአፌቅ ከተማ ትወጋቸዋለህ።”


ከዚህም በኋላ የእስራኤል ንጉሥ ዮአስ ቤንሀዳድን ሦስት ጊዜ ድል ነሥቶ በአባቱ በኢዮአካዝ ዘመነ መንግሥት ቤንሀዳድ ይዞአቸው የነበሩትን ከተሞች አስመለሰ።


አቢያና ሠራዊቱ እስራኤላውያንን ድል አድርገው ከፍ ያለ ጒዳት አደረሱባቸው፤ በዚህ ጦርነት ከእስራኤል አምስት መቶ ሺህ ምርጥ ወታደሮች ተገደሉ።


እግዚአብሔር ለዘለዓለም ንጉሥ ሆኖ ይኖራል፤ ለሌሎች አማልክት የሚሰግዱ ሕዝቦች ግን ከምድሩ ይጠፋሉ።


በዚያው ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ወደ አሦራውያን ሰፈር አልፎ መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ ወታደሮችን ገደለ፤ በማግስቱ በማለዳ ሰዎች በሚነቁበት ጊዜ ሁሉም ሞተው ተገኙ።


በሰባተኛው ቀን ጎሕ ሲቀድ ማልደው ተነሥተው በዚሁ ተመሳሳይ ሁኔታ ከተማይቱን ሰባት ጊዜ ዞሩአት፤ ከተማይቱን ሰባት ጊዜ የዞሩበት ቀን ይህ ብቻ ነበር።


ፍልስጥኤማዊውም ለአርባ ቀኖች በፊታቸው እየመጣ ቆሞ ይፎክር ነበር።


跟着我们:

广告


广告