Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 20:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ንጉሥ አክዓብ መልእክተኞቹን “ ‘እውነተኛ ወታደር መደንፋት የሚገባው ከጦርነት ድል በኋላ እንጂ ከጦርነት በፊት አይደለም’ ብላችሁ ለንጉሥ ቤንሀዳድ ንገሩት” ሲል መለሰላቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የእስራኤልም ንጉሥ፣ “ ‘ታጥቆ ለጦርነት የሚወጣ ሰው የጦር ትጥቁን እንደ ፈታ ሰው መደንፋት የለበትም’ ብላችሁ ንገሩት” አላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ንጉሥ አክዓብ መልእክተኞቹን “እውነተኛ ወታደር መደንፋት የሚገባው ከጦርነት ድል በኋላ እንጂ ከጦርነት በፊት አይደለም ብላችሁ ለንጉሥ ቤንሀዳድ ንገሩት” ሲል መለሰላቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በከ​ተ​ማ​ውም የተ​ቀ​መ​ጡት የከ​ተ​ማው ሰዎ​ችና ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ አለ​ቆ​ችም ኤል​ዛ​ቤል እን​ዳ​ዘ​ዘ​ቻ​ቸ​ውና ወደ እነ​ርሱ በተ​ላ​ከው ደብ​ዳቤ እንደ ተጻ​ፈው እን​ዲሁ አደ​ረጉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በከተማውም የተቀመጡት የከተማው ሰዎችና ሽማግሌዎች ከበርቴዎችም ኤልዛቤል እንዳዘዘቻቸውና ወደ እነርሱ በተላከው ደብዳቤ እንደ ተጻፈ እንዲሁ አደረጉ።

参见章节 复制




1 ነገሥት 20:11
12 交叉引用  

ሞአባውያንም ሦስቱ ነገሥታት አደጋ ሊጥሉባቸው መምጣታቸውን በሰሙ ጊዜ፥ ከሽማግሌ እስከ ወጣት መሣሪያ መያዝ የሚችሉ ሰዎች ሁሉ ተጠርተው በመውጣት በጠረፉ ላይ ተጠባበቁ።


ከቻልክ እስቲ እጅህን በላዩ ላይ አሳርፍበት። ከእርሱ ጋር የምታደርገውን ትግል በፍጹም አትረሳውም፤ ዳግመኛም ከእርሱ ጋር ለመታገል አትሞክርም።


ጊዜ የሚያመጣውን ነገር ስለማታውቅ ነገ በሚሆነው ነገር አትመካ።


በዚህ ዓለም የተመለከትኩት ሌላም ነገር አለ፤ ይኸውም ፈጣን ሯጮች በአሸናፊነት አይወጡም፤ ጀግኖችም በጦርነት ድል አያደርጉም፤ ጠቢባን የዕለት እንጀራን፥ ብልኆች ሀብትን አያገኙም፤ ችሎታ ያላቸውም ሰዎች በማዕርግ አያድጉም፤ ነገር ግን ሁሉንም ጊዜና ዕድል ያጋጥማቸዋል፤


የግብጽን ንጉሥ “በዕድሉ የማይጠቀም ለፍላፊ፥” በሚል አዲስ ስም ይጠሩታል፤


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ጠቢብ በጥበቡ፥ ብርቱ ሰውም በኀይሉ፥ ባለጸጋም በሀብቱ አይመካ፤


ጴጥሮስም “ዶሮ ሳይጮህ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” ብሎ ኢየሱስ የተናገረው ቃል ትዝ አለው። ወደ ውጭም ወጣና ምርር ብሎ አለቀሰ።


ዮናታን ጋሻ ጃግሬ የሆነውን ወጣት “ና ወደ እነዚያ ወደ አልተገረዙት ወገኖች የጦር ሰፈር እንሻገር እግዚአብሔር ይረዳን ይሆናል፤ በብዙም ሆነ በጥቂት እግዚአብሔር ማዳን አይሳነውም” አለው።


跟着我们:

广告


广告