Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 2:46 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

46 ከዚህም በኋላ ለዮዳሄ ልጅ ለበናያ ሺምዒን እንዲገድል ትእዛዝ አስተላለፈ፤ በናያም ሄዶ ሺምዒን ገደለው፤ በዚህም ዐይነት መንግሥቱ በሰሎሞን እጅ የጸና ሆነ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

46 ከዚያም ንጉሡ የዮዳሄን ልጅ በናያስን አዘዘው፤ በናያስም ወጣ፤ ሳሚንም መትቶ ገደለው። በዚህ ጊዜም መንግሥቱ በሰሎሞን እጅ ጸና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

46 ከዚህም በኋላ ለዮዳሄ ልጅ ለበናያ ሺምዒን እንዲገድል ትእዛዝ አስተላለፈ፤ በናያም ሄዶ ሺምዒን ገደለው፤ በዚህም ዓይነት መንግሥቱ በሰሎሞን እጅ የጸና ሆነ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

46 ሰሎ​ሞ​ንም የዮ​ዳ​ሄን ልጅ በን​ያ​ስን አዘ​ዘው፤ ወጥ​ቶም ገደ​ለው። የሰ​ሎ​ሞ​ንም መን​ግ​ሥት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ጸና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

46 ንጉሡም የዮዳሄን ልጅ በናያስን አዘዘው፤ ወጥቶም ወደቀበት፤ ሞተም። መንግሥትም በሰሎሞን እጅ ጸና።

参见章节 复制




1 ነገሥት 2:46
7 交叉引用  

ሰሎሞንም በአባቱ እግር ተተክቶ ነገሠ፤ የመንግሥቱም ሥልጣን እጅግ የጸና ሆነ።


ስለዚህም አዶንያስን እንዲገድለው ንጉሥ ሰሎሞን ለዮዳሄ ልጅ ለበናያ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ በናያም ሄዶ አዶንያስን ገደለው።


ስለዚህ በናያ በታዘዘው መሠረት ኢዮአብን ገደለው፤ በቤቱም አጠገብ በሚገኘው በረሓ ተቀበረ።


እኔን ግን እግዚአብሔር ይባርከኛል፤ የዳዊት መንግሥትም ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል።”


የዳዊት ልጅ ንጉሥ ሰሎሞን መንግሥቱን አጠናከረ፤ እግዚአብሔር አምላኩም ባረከው፤ እጅግ በጣም ገናናም አደረገው።


ከንጉሥ ፊት ክፉ ሰዎችን አስወግድ፤ መንግሥቱም በፍትሕ ጸንታ ትኖራለች።


ንጉሥ ፍትሕ እንዳይጓደል በሚያደርግበት ጊዜ ሀገሩን ያረጋጋል፤ ሕዝብን የሚበዘብዝ መሪ ግን ሀገሩን ወደ ጥፋት ያደርሳል።


跟着我们:

广告


广告