Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 2:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እግዚአብሔር በአባቴ በዳዊት ዙፋን ላይ አስቀምጦ መንግሥቴን የጸና አድርጎልኛል፤ ይህን መንግሥት ለእኔና ለዘሮቼ በመስጠት ቃሉን ጠብቆአል፤ እንግዲህ አዶንያስ በዚህ በዛሬው ቀን በሞት እንደሚቀጣ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ!”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 አሁንም በሚገባ ያጸናኝ፤ በአባቴ በዳዊት ዙፋን ያስቀመጠኝና በሰጠውም ተስፋ መሠረት ሥርወ መንግሥትን የመሠረተልኝ ሕያው እግዚአብሔርን አዶንያስ ዛሬ ይሞታል!”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 እግዚአብሔር በአባቴ በዳዊት ዙፋን ላይ አስቀምጦ መንግሥቴን የጸና አድርጎልኛል፤ ይህን መንግሥት ለእኔና ለዘሮቼ በመስጠት ቃሉን ጠብቆአል፤ እንግዲህ አዶንያስ በዚህ በዛሬው ቀን በሞት እንደሚቀጣ በሕያው ጌታ ስም እምላለሁ!”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 አሁ​ንም ያጸ​ናኝ፥ በአ​ባ​ቴም በዳ​ዊት ዙፋን ላይ ያስ​ቀ​መ​ጠኝ፥ እንደ ተና​ገ​ረ​ውም ቤትን የሠ​ራ​ልኝ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ዛሬ አዶ​ን​ያስ ፈጽሞ ይገ​ደ​ላል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 አሁንም ያጸናኝ፥ በአባቴም በዳዊት ዙፋን ላይ ያስቀመጠኝ፥ እንደ ተናገረውም ቤትን የሠራልኝ ሕያው እግዚአብሔርን! ዛሬ አዶንያስ ፈጽሞ ይገደላል፤” ብሎ በእግዚአብሔር ማለ።

参见章节 复制




1 ነገሥት 2:24
19 交叉引用  

አንተ ለእኔ ስላልታዘዝክ የኦርዮን ሚስት ስለ ወሰድክ፥ እነሆ ከቤትህ በሰይፍ የሚገደል አይጠፋም፤


የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ ለአገልጋይህ ቤት እሠራለሁ ብለህ ስለ ገለጥክለት አገልጋይህ ይህን ጸሎት ወደ አንተ ለማቅረብ ድፍረት አግኝቶአል።


በዚህም ጊዜ እንዲህ አላት፥ “ከደረሰብኝ መከራ ሁሉ በታደገኝ በሕያው እግዚአብሔር ስም ቃል እገባልሻለሁ፤


እነሆ ሰሎሞን ነግሦ በንጉሣዊ ዙፋን ላይ ተቀምጦአል፤


ንጉሥ ሰሎሞንም “አካሄዱን ካሳመረ ከራስ ጠጒሩ አንዲት እንኳ አትነካበትም፤ ክፉ ሆኖ ከተገኘ ግን ይሞታል” ሲል መለሰ፤


አምላክህ እግዚአብሔር ይመስገን! እርሱ አንተን መርጦ የእስራኤል ንጉሥ በማድረግ በአንተ መደሰቱን ገልጦልሃል፤ ለእስራኤል ያለውም ፍቅር ዘለዓለማዊ ስለ ሆነ ጽድቅና ፍትሕ ጸንቶ እንዲኖር ታደርግ ዘንድ የእስራኤል ንጉሥ አድርጎሃል።”


እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ ያለፈው ሁሉ በፊትህ የማይበቃ ሆኖ ስለ አገልጋይህ ቤት ለሚመጣው ሩቅ ዘመን አሁንም እንደገና እኔን እንደ ትልቅ ባለማዕርግ አድርገህ ተመለከትከኝ።


“አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ ስለ እኔና ስለ ዘሮቼ የተናገርከውን የተስፋ ቃል ሁሉ ፈጽም፤ አደርጋለሁ ያልከውንም ሁሉ አድርግ፤


ለእኔ ቤተ መቅደስ የሚሠራልኝ እርሱ ነው፤ እርሱ ልጅ ይሆነኛል፤ እኔም አባት እሆነዋለሁ፤ መንግሥቱም በእስራኤል ላይ ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል።’ ”


በዚህ ዐይነት ሰሎሞን በአባቱ እግር ተተክቶ እግዚአብሔር ባጸናው ዙፋን ላይ ተቀመጠ፤ እርሱም ሁሉ ነገር የተሳካለት ንጉሥ ሆነ፤ መላውም የእስራኤል ሕዝብ ታዘዙለት፤


እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፥ የቤት ሠሪዎች ድካም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፥ የከተማ ጠባቂዎች ትጋት ከንቱ ነው።


የንጉሥ ቊጣ እንደሚያገሣው አንበሳ ያስፈራል፤ የእርሱንም ቊጣ የሚያነሣሣ በራሱ ላይ የሞት ፍርድ እንደ ፈረደ ይቈጠራል።


ጌታዬ፥ አንተ የእግዚአብሔርን ጦርነት እየተዋጋህ ነው፤ በምትኖርበትም ዘመን ሁሉ ምንም ዐይነት ክፉ ነገር ማድረግን ስለማትፈልግ ስለ ፈጸምኩት በደል እባክህ ይቅር በለኝ፤ እግዚአብሔር አንተንና ዘሮችህን ለዘለዓለም ያነግሣል፤


跟着我们:

广告


广告