Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 17:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እግዚአብሔር በኤልያስ አማካይነት በሰጠው ተስፋ መሠረት ዱቄቱ ከማኖሪያው ዕቃ፥ ዘይቱም ከማሰሮው አላለቀም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 በኤልያስ በተነገረው የእግዚአብሔር ቃል መሠረት ከማድጋው ዱቄት አልጠፋም፤ ከማሰሮውም ዘይት አላለቀም ነበርና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ጌታ በኤልያስ አማካይነት በሰጠው ተስፋ መሠረት ዱቄቱ ከማኖሪያው ዕቃ፥ ዘይቱም ከማሰሮው አላለቀም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 በአ​ገ​ል​ጋዩ በኤ​ል​ያ​ስም ቃል እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ዱቄቱ ከማ​ድ​ጋው አል​ተ​ጨ​ረ​ሰም፤ ዘይ​ቱም ከማ​ሰ​ሮው አል​ጐ​ደ​ለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 በኤልያስም አማካይነት እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል ዱቄቱ ከማድጋው አልተጨረሰም፤ ዘይቱም ከማሰሮው አልጎደለም።

参见章节 复制




1 ነገሥት 17:16
13 交叉引用  

የእግዚአብሔርም ነቢይ በእግዚአብሔር ስም በተናገረው የትንቢት ቃል መሠረት በእግዚአብሔር የተሰጠውም ምልክት ተፈጸመ፤ መሠዊያው ወዲያውኑ ተሰባብሮ ወደቀ፤ ዐመዱም መሬት ላይ ፈሰሰ።


በዚህም ዐይነት እግዚአብሔር በነቢዩ ኢዩ አማካይነት በባዕሻ ላይ ባናገረው ትንቢት መሠረት ዚምሪ የባዕሻን ቤተሰብ በሙሉ ፈጀ።


እርስዋም ሄዳ ኤልያስ እንደ ነገራት አደረገች፤ በዚህም ዐይነት እርስዋ፥ ቤተሰብዋና ኤልያስም ለብዙ ቀን የሚሆን በቂ ምግብ አገኙ።


ከጥቂት ጊዜም በኋላ የዚያች ባልዋ የሞተባት ሴት ልጅ ታመመ፤ ሕመሙም እየባሰበት ስለ ሄደ በመጨረሻ ሞተ፤


ሠረገላውም በሰማርያ ኲሬ ታጠበ፤ እግዚአብሔርም አስቀድሞ በተናገረው መሠረት ደሙን ውሾች ላሱት፤ በዚያም ኲሬ ጋለሞታዎች ታጠቡበት።


እግዚአብሔር በኤልያስ አማካይነት በተናገረውም ቃል መሠረት አካዝያስ ሞተ፤ አካዝያስ ወንዶች ልጆች ስላልነበሩት በእርሱ እግር ተተክቶ ወንድሙ ኢዮራም ነገሠ፤ ይህም የሆነው የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዮራም በይሁዳ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ነበር።


ስለዚህም ንዕማን የእግዚአብሔር ሰው ባዘዘው መሠረት ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ወርዶ ሰባት ጊዜ በመነከር ታጠበ፤ ከበሽታውም ፈጽሞ ነጻ፤ ሥጋውም እንደ ትንሽ ልጅ ገላ በመታደስ ፍጹም ጤናማ ሆነ፤


ኢየሱስ ወደ እነርሱ ተመልክቶ “ይህ ነገር ለሰው የማይቻል ነው፤ ለእግዚአብሔር ግን ሁሉም ይቻለዋል” አለ።


በዚያም ኢየሱስ በማእድ ተቀምጦ ሳለ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ ሽቶ የሞላበት የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ ወደ እርሱ ቀረበች፤ ሽቶውንም በራሱ ላይ አፈሰሰችው።


ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም።”


አንቺ ጌታ የተናገረውን ሁሉ የሚፈጽም መሆኑን በማመንሽ ምንኛ የተባረክሽ ነሽ!”


跟着我们:

广告


广告