1 ነገሥት 13:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 ሽማግሌው ነቢይ ይህን በሰማ ጊዜ “ያ ሰው የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ያልጠበቀው ነቢይ መሆን አለበት! ስለዚህም እግዚአብሔር ለአንበሳ አሳልፎ ሰጥቶታል ማለት ነው” አለ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም26 ያም ከመንገድ የመለሰው ነቢይ ይህን ሲሰማ፣ “ይህ የእግዚአብሔርን ቃል ያቃለለው ያ የእግዚአብሔር ሰው ነው፤ እግዚአብሔር ባስጠነቀቀው ቃል መሠረት አሳልፎ ሰጥቶት አንበሳ ሰብሮ ገድሎታል” አለ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 ያም ከመንገድ የመለሰው ነቢይ ይህን በሰማ ጊዜ “ይህ የጌታን ቃል ያቀለለው ያ ጌታ ሰው ነው፤ ጌታ ባስጠነቀቀው መሠረት አሳልፎ ሰጥቶት አንበሳ ሰብሮ ገድሎታል” አለ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 ያም ከመንገድ የመለሰው ነቢይ ያን ሰምቶ፥ “በእግዚአብሔር ቃል ላይ ያመፀ ያ የእግዚአብሔር ሰው ነው” አለ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26 ያም ከመንገድ የመለሰው ነቢይ ያን በሰማ ጊዜ “በእግዚአብሔር አፍ ላይ ያመፀ ያ የእግዚአብሔር ሰው ነው፤ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው ቃል፥ እግዚአብሔር ለአንበሳ አሳልፎ ሰጥቶታል፤ ሰብሮም ገድሎታል፤” አለ። 参见章节 |