Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 13:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ከይሁዳ የመጣው የእግዚአብሔር ነቢይ የሄደበትን መንገድ አቅጣጫ ይዞ ተከተለው፤ በአንድ የወርካ ዛፍ ሥር ተቀምጦም አገኘው። ሽማግሌውም “ከይሁዳ የመጣኸው የእግዚአብሔር ነቢይ አንተ ነህን?” ሲል ጠየቀው። እርሱም “አዎ እኔ ነኝ” ሲል መለሰለት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እየጋለበ ያን የእግዚአብሔር ሰው ተከተለው። ከዚያም በአንድ የወርካ ዛፍ ሥር ተቀምጦ አገኘውና፣ “ከይሁዳ የመጣኸው የእግዚአብሔር ሰው አንተ ነህን?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፣ “አዎን እኔ ነኝ” ብሎ መለሰለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ከይሁዳ የመጣው የእግዚአብሔር ሰው የሄደበትን መንገድ አቅጣጫ ይዞ ተከተለው፤ በአንድ የባሉጥ ዛፍ ሥር ተቀምጦም አገኘው። ሽማግሌውም “ከይሁዳ የመጣኸው የእግዚአብሔር ሰው አንተ ነህን?” ሲል ጠየቀው። እርሱም “አዎ እኔ ነኝ” ሲል መለሰለት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሰው ተከ​ት​ሎት ሄደ፤ ከዛፍ በታ​ችም ተቀ​ምጦ አገ​ኘ​ውና፥ “ከይ​ሁዳ የመ​ጣህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው አንተ ነህን?” አለው። እር​ሱም፥ “አዎ፥ እኔ ነኝ” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ከእግዚአብሔርም ሰው በኋላ ሄደ፤ በአድባርም ዛፍ በታች ተቀምጦ አገኘውና “ከይሁዳ የመጣህ የእግዚአብሔር ሰው አንተ ነህን?” አለው። እርሱም “እኔ ነኝ፤” አለ።

参见章节 复制




1 ነገሥት 13:14
9 交叉引用  

አብራም በሴኬም ወደሚገኘው ቅዱስ ስፍራ ወደ ሞሬ ዛፍ እስኪደርስ ድረስ ተጓዘ፤ በዚያን ጊዜ ከነዓናውያን በዚያች ምድር ይኖሩ ነበረ።


ከዚህም በኋላ እርሱ “አህያዬን ጫኑልኝ!” አላቸው፤ ልጆቹም አህያውን ጭነውለት ሽማግሌው ነቢይ በአህያው ላይ ተቀምጦ፥


ሽማግሌውም “ወደ ቤቴ መጥተህ ከእኔ ጋር እህል ብላ” አለው።


ኤልያስ አንድ ቀን ሙሉ በበረሓ ተጓዘ፤ ከዚህ በኋላ ጒዞውን ቆም አድርጎ፥ በአንድ የክትክታ ዛፍ ጥላ ሥር ተቀመጠ፤ ሞቱንም በመመኘት “እግዚአብሔር ሆይ! አሁንስ ይብቃኝ፤ ከቀድሞ አባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ!” ሲል ጸለየ።


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “የእኔ ምግብ የላከኝን ፈቃድ ማድረግና ሥራውንም መፈጸም ነው።


በዚያም የያዕቆብ የውሃ ጒድጓድ ነበረ፤ ኢየሱስ መንገድ ከመሄድ የተነሣ ስለ ደከመው በጒድጓዱ አጠገብ ተቀመጠ፤ ጊዜውም ወደ ስድስት ሰዓት ገደማ ነበረ።


ብዙ ሥራና ድካም ነበረብኝ፤ ብዙ ጊዜ እንቅልፍ አጥቻለሁ፤ በራብና በውሃ ጥም ተጨንቄአለሁ፤ ብዙ ጊዜም የምግብ እጦት ደርሶብኛል፤ ብርድና መራቆትም ደርሶብኛል።


跟着我们:

广告


广告