Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 1:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 “የራስሽንና የልጅሽን የሰሎሞንን ሕይወት ለማትረፍ እንድትችይ ልምከርሽ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 አሁንም የራስሽንና የልጅሽን የሰሎሞንን ሕይወት እንዴት ማዳን እንደምትችዪ ልምከርሽ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 አሁንም ነዪ፥ የልጅሽን የሰሎሞንን ነፍስና የአንቺን ነፍስ እንድታድኝ እመክርሻለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 አሁ​ንም ነዪ፤ የል​ጅ​ሽን የሰ​ሎ​ሞ​ንን ነፍ​ስና የአ​ን​ቺን ነፍስ እን​ድ​ታ​ድኚ እመ​ክ​ር​ሻ​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 አሁንም ነዪ፤ የልጅሽን የሰሎሞንን ነፍስና የአንቺን ነፍስ እንድታድኝ እመክርሻለሁ።

参见章节 复制




1 ነገሥት 1:12
14 交叉引用  

ካወጡአቸውም በኋላ ከመላእክቱ አንዱ “ሕይወታችሁን አድኑ! ወደ ኋላ አትመልከቱ! በሸለቆው ውስጥ አትዘግዩ፤ እንዳትሞቱ ወደ ተራራው ሽሹ!” አላቸው።


ወደ ንጉሥ ዳዊት ገብተሽ ‘ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ነግሦ በዙፋኔ ይቀመጣል’ ብለህ ለአገልጋይህ በመሐላ ቃል ገብተህልኝ አልነበረምን? ታዲያ፥ አሁን አዶንያስ እንዴት ሊነግሥ ቻለ? ብለሽ ንገሪው”።


ይህን ባታደርግ ግን አንተ ከሞትህ በኋላ ወዲያውኑ ልጄ ሰሎሞንና እኔ እንደ በደለኞች እንቈጠራለን።”


የንጉሥ አካዝያስ እናት ዐታልያ የልጅዋን መገደል እንደ ሰማች ወዲያውኑ የይሁዳ ንጉሣውያን ቤተሰብ አባላት በሙሉ እንዲገደሉ ትእዛዝ ሰጠች።


ኢዮራም መንግሥቱን ካጠናከረ በኋላ ወንድሞቹን በሙሉ እንዲሁም አንዳንድ የእስራኤል ባለሥልጣኖችን ገደለ።


የንጉሥ አካዝያስ እናት ዐታልያ የልጅዋን መገደል እንደሰማች ወዲያውኑ የይሁዳ ንጉሣውያን ቤተሰብ አባሎች በሙሉ እንዲገደሉ ትእዛዝ አስተላለፈች።


አማካሪ የሌለው መንግሥት ይወድቃል፤ ብዙ አማካሪዎች ሲኖሩ ግን ዋስትና ይገኛል።


መልካም ምክርን ብትቀበል ሁሉ ነገር ይሳካልሃል፤ ምክርን ባትቀበል ግን ምንም ነገር አይሳካልህም።


መልካም ምክርን ብትቀበል ሁሉ ነገር ይሳካልሃል፤ ስለዚህ መልካም ምክር ሳትቀበል ወደ ጦርነት አትሂድ።


ሽቶና መልካም መዓዛ ያለው ቅባት ሰውን ደስ እንደሚያሰኝ የወዳጅ ምክርም እንዲሁ ደስ ያሰኛል።


እኔም “እውነቱን ብነግርህ አትገድለኝምን? መቼም ብመክርህ ልታዳምጠኝ አትፈልግም” አልኩት።


ገበሬዎቹ ግን ልጁን ባዩ ጊዜ ‘ይህማ ወራሹ ነው፤ ኑ እንግደለውና ርስቱን እኛ እንውረስ!’ ተባባሉ።


በዚህ ጊዜ ጳውሎስ መቶ አለቃውንና ወታደሮቹን “እነዚህ መርከበኞች በመርከቡ ላይ ዐርፈው ካልተቀመጡ እናንተ ለመዳን አትችሉም” አላቸው።


ወደ አባቱ ቤት ወደ ዖፍራም ሄዶ የጌዴዎን ልጆች የሆኑትን ሰባውን ወንድሞቹን በአንድ ድንጋይ ላይ ዐረዳቸው፤ የጌዴዎን መጨረሻ ልጅ ኢዮአታም ግን ተደብቆ ስለ ነበር ከሞት ተረፈ፤


跟着我们:

广告


广告