1 ዮሐንስ 2:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ልጆች ሆይ፥ አብን ስላወቃችሁት ጽፌላችኋለሁ። አባቶች ሆይ፥ ከመጀመሪያው የነበረውን ስላወቃችሁት ጽፌላችኃለሁ። ወጣቶች ሆይ፥ ብርቱዎች ስለ ሆናችሁና የእግዚአብሔር ቃል በልባችሁ ስለሚኖር፥ ሰይጣንንም ስላሸነፋችሁ ጽፌላችኋለሁ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም14 አባቶች ሆይ፤ ከመጀመሪያ ያለውን እርሱን ዐውቃችሁታልና፣ እጽፍላችኋለሁ። ጐበዛዝት ሆይ፤ ብርቱዎች ስለ ሆናችሁ፣ የእግዚአብሔር ቃል በእናንተ ስለሚኖር፣ ክፉውንም ስላሸነፋችሁ፣ እጽፍላችኋለሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ልጆች ሆይ፥ አብን አውቃችሁታልና ጽፌላችኋለሁ። አባቶች ሆይ፥ ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃችሁታልና ጽፌላችኋለሁ። ወጣቶች ሆይ፥ ብርቱዎች ስለ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም ቃል በውስጣችሁ ስለሚኖር ክፉውንም ስለ አሸነፋችሁ ጽፌላችኋለሁ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 አባቶች ሆይ፥ ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ። ጐበዞች ሆይ፥ ብርቱዎች ስለ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም ቃል በእናንተ ስለሚኖር ክፉውንም ስለ አሸነፋችሁ እጽፍላችኋለሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 አባቶች ሆይ፥ ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ። ጐበዞች ሆይ፥ ብርቱዎች ስለ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም ቃል በእናንተ ስለሚኖር ክፉውንም ስለ አሸነፋችሁ እጽፍላችኋለሁ። 参见章节 |