1 ቆሮንቶስ 7:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም35 እኔ ይህን የምላችሁ በወጥመድ ውስጥ ገብታችሁ እንድትቸገሩ ብዬ ሳይሆን እንድትጠቀሙ ብዬ ነው፤ ምኞቴም እናንተ በተገቢው ሁኔታ እንድትኖሩና አሳባችሁ ሳይባክን በሙሉ ልባችሁ ጌታን እንድታገለግሉ ነው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም35 ይህንም የምለው ለእናንተ የሚበጃችሁን ነገር በማሰብ እንጂ ላስጨንቃችሁ አይደለም፤ ዐላማዬም ልባችሁ ሳይከፈል በጌታ ጸንታችሁ በአግባብ እንድትኖሩ ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)35 ይህንም ለራሳችሁ ጥቅም እላለሁ፤ በአግባብ እንድትኖሩ ሳትባክኑም ለጌታ በጽናት እንድታገለግሉ ነው እንጂ ላጠምዳችሁ ብዬ አይደለም። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)35 ይህንም የምላችሁ እንዲጠቅማችሁ ነው፤ ላጠምዳችሁ ግን አይደለም፤ ኑሮአችሁ አንድ ወገን እንዲሆንና እግዚአብሔርን ያለመጠራጠር እንድታገለግሉት ነው እንጂ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)35 ይህንም ለራሳችሁ ጥቅም እላለሁ፤ በአገባብ እንድትኖሩ ሳትባክኑም በጌታ እንድትጸኑ ነው እንጂ ላጠምዳችሁ ብዬ አይደለም። 参见章节 |