Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ቆሮንቶስ 7:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ነገር ግን አንተ ሚስት ብታገባ ኃጢአት ይሆንብሃል ማለት አይደለም፤ እንዲሁም አንዲት ልጃገረድ ባል ብታገባ ኃጢአት ይሆንባታል ማለት አይደለም፤ ይሁን እንጂ የሚያገቡ ሰዎች በዚህ ዓለም ብዙ የኑሮ ችግር ይገጥማቸዋል፤ የእኔም ምኞት ከዚህ ችግር እንድትድኑ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ብታገባ ግን ኀጢአት አልሠራህም፤ ድንግሊቱም ብታገባ ኀጢአት አላደረገችም። ነገር ግን የሚያገቡ ሰዎች በዚህ ዓለም ብዙ ችግር ይገጥማቸዋል፤ እኔም ይህ እንዳይደርስባችሁ እወድዳለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ብታገባ ግን ኃጢአት አትሠራም፤ ድንግሊቱም ብታገባ ኃጢአት አትሠራም፤ ነገር ግን እንዲህ በሚያደርጉ በሥጋቸው ላይ መከራ ይገጥማቸዋል፤ እኔም ከዚያ ባስጣልኳችሁ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ብታ​ገ​ባም ኀጢ​አት አይ​ሆ​ን​ብ​ህም፤ ድን​ግ​ሊ​ቱም ባል ብታ​ገባ ኀጢ​አት አይ​ሆ​ን​ባ​ትም፤ ያገቡ ግን ለራ​ሳ​ቸው ድካ​ምን ይሻሉ፤ እኔም ይህን የም​ላ​ችሁ ስለ​ማ​ዝ​ን​ላ​ችሁ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ብታገባ ግን ኃጢአት አትሠራም ድንግሊቱም ብታገባ ኃጢአት አትሠራም፤ ነገር ግን እንዲህ በሚያደርጉ በሥጋቸው ላይ መከራ ይሆንባቸዋል፥ እኔም እራራላችሁ ነበር።

参见章节 复制




1 ቆሮንቶስ 7:28
7 交叉引用  

እኔ ግን “በዝሙት ምክንያት ካልሆነ በቀር፥ ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ እንድታመነዝር ያደርጋታል፤ የተፈታችውንም የሚያገባ ሁሉ አመንዝራ ይሆናል” እላችኋለሁ።


አሁን ያለንበት ጊዜ የችግር ጊዜ ስለ ሆነ ሳያገቡ በብቸኝነት መኖር መልካም ይመስለኛል፤


ሆኖም ሚስት አግብተህ እንደ ሆነ ለመፍታት አትፈልግ፤ ሚስት አላገባህ እንደ ሆነ ለማግባት አትፈልግ።


ወንድሞች ሆይ! እኔ የምላችሁ እንዲህ ነው፤ ዘመኑ አጥሮአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስት ያለችው ሚስት እንደሌለችው ሆኖ ይኑሩ። ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌሉአቸው ሆነው ይኑር።


እኔ ወደ ቆሮንቶስ ተመልሼ ያልመጣሁበት ምክንያት እናንተን እንዳላሳዝናችሁ ለእናንተ በመራራት ነው፤ ለዚሁም እግዚአብሔር ምስክሬ ነው፤


ጋብቻ በሁሉ ዘንድ የተከበረ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን እግዚአብሔር ስለሚፈርድባቸው ባልና ሚስት ታማኝነትን በማጒደል ጋብቻን አያርክሱ።


跟着我们:

广告


广告