Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ቆሮንቶስ 7:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ስላላገቡ ሰዎች ከጌታ የተቀበልኩት ትእዛዝ የለኝም፤ ነገር ግን በጌታ ምሕረት እምነት የሚጣልብኝ እንደ መሆኔ መጠን የራሴ ሐሳብ ከዚህ ቀጥሎ ያለው ነው፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ስለ ደናግል፣ ከጌታ የተቀበልሁት ትእዛዝ የለኝም፤ ይሁን እንጂ፣ ከጌታ ምሕረት የተነሣ እንደ ታማኝ ሰው፣ ምክሬን እሰጣለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ደናግልን በተመለከተ የጌታ ትእዛዝ የለኝም፤ ነገር ግን በጌታ ምሕረት የታመንሁ እሆን ዘንድ ምክሬን እለግሳችሀለሁ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ስለ ደና​ግ​ልም የም​ነ​ግ​ራ​ችሁ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ አይ​ደ​ለም፤ ታማኝ እን​ድ​ሆን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅር ያለኝ እንደ መሆኔ ምክ​ሬን እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ እንጂ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ስለ ደናግልም የጌታ ትእዛዝ የለኝም፥ ነገር ግን የታመንሁ እሆን ዘንድ ከጌታ ምሕረትን የተቀበልሁ እንደ መሆኔ ምክር እመክራለሁ።

参见章节 复制




1 ቆሮንቶስ 7:25
15 交叉引用  

ጐልማሶች ሁሉ በእሳት ተቃጥለው ሞቱ፤ ልጃገረዶችም የጋብቻቸውን ደስታ ሳያዩ ተቀጩ።


ነገር ግን እኔ አሁን የሆንኩትን ሆኜ የምገኘው በእግዚአብሔር ጸጋ ነው፤ የተሰጠኝም ጸጋ ያለ ፍሬ አልቀረም፤ እንዲያውም ከሌሎቹ ይበልጥ በሥራ ደክሜአለሁ፤ ነገር ግን ይህን ያደረገው ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም።


ባለ ዐደራዎችም ታማኞች ሆነው መገኘት አለባቸው።


ላገቡት ግን የምሰጠው ትእዛዝ ይህ ነው፤ ይህም ትእዛዝ የጌታ ነው እንጂ የእኔ አይደለም፤ ያገባች ሴት ከባልዋ አትለይ፤


ለሌሎቹ ግን ጌታ ሳይሆን እኔ ራሴ የምለው እንዲህ ነው፤ አንድ ክርስቲያን ሰው ክርስቲያን ያልሆነች ሚስት ብትኖረውና አብራው ለመኖር ብትፈልግ አይፍታት።


ነገር ግን አንተ ሚስት ብታገባ ኃጢአት ይሆንብሃል ማለት አይደለም፤ እንዲሁም አንዲት ልጃገረድ ባል ብታገባ ኃጢአት ይሆንባታል ማለት አይደለም፤ ይሁን እንጂ የሚያገቡ ሰዎች በዚህ ዓለም ብዙ የኑሮ ችግር ይገጥማቸዋል፤ የእኔም ምኞት ከዚህ ችግር እንድትድኑ ነው።


በዚህ ሁኔታ ሐሳቡ በሁለት ተከፍሎአል ማለት ነው። እንዲሁም ባል ያላገባች ሴት ወይም ልጃገረድ በሥጋዋና በነፍስዋ ተቀድሳ የጌታ ለመሆን ስለምትፈልግ ሐሳቧ የሚያተኲረው ጌታን በሚመለከት ሥራ ነው። ያገባች ሴት ግን ባልዋን ለማስደሰት ስለምትፈልግ የምታስበው የዓለምን ነገር ነው።


በእኔ አስተያየት ግን ባል ሳታገባ ብቻዋን ብትሆን ይበልጥ ተደስታ ትኖራለች፤ እኔም የእግዚአብሔር መንፈስ ያለኝ ይመስለኛል።


ይህን ግን የምላችሁ እንደምክር ነው እንጂ እንደ ትእዛዝ አይደለም።


እንደዚሁ በትምክሕት ስናገር የምናገረው እንደ ጌታ ፈቃድ ሳይሆን እንደ ሞኝ ሆኜ ነው።


እኛ የእግዚአብሔርን ቃል እንደ ንግድ ዕቃ እንደሚቸረችሩት እንደ ብዙዎቹ አይደለንም፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላኩ ቅን መልእክተኞች በክርስቶስ ሆነን በእግዚአብሔር ፊት እንናገራለን።


跟着我们:

广告


广告