1 ቆሮንቶስ 6:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 “ምግብ ለሆድ፥ ሆድም ለምግብ ነው፤” ታዲያ፥ እግዚአብሔር ምግብንም፥ ሆድንም ያጠፋቸዋል፤ ነገር ግን ሰውነታችን ለጌታ ኢየሱስ፥ ጌታ ኢየሱስም ለሰውነታችን ስለ ሆነ ሰውነታችንን ለዝሙት ማዋል አይገባንም። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም13 ደግሞም፣ “ምግብ ለሆድ ነው፤ ሆድም ለምግብ ነው፤” እግዚአብሔር ግን ሁለቱንም ያጠፋቸዋል። ሰውነት ለጌታ ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም፤ ጌታም ለሰውነት ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 “ምግብ ለሆድ ነው፤ ሆድም ለምግብ ነው፤” እግዚአብሔር ግን ይህንም ያንም ያጠፋቸዋል። ሰውነት ግን ለጌታ ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም፤ ጌታም ለሰውነት ነው፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 መብል ለሆድ ነው ፤ ሆድም ለመብል ነው፤ እግዚአብሔር ግን ሁለቱንም ይሽራቸዋል፤ ሥጋችሁም ለእግዚአብሔር ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም፤ እግዚአብሔርም ለሥጋችሁ ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 መብል ለሆድ ነው፥ ሆድም ለመብል ነው፤ እግዚአብሔር ግን ይህንም ያንም ያጠፋቸዋል። ሥጋ ግን ለጌታ ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም፤ ጌታም ለሥጋ ነው፤ 参见章节 |