1 ቆሮንቶስ 6:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 ከእናንተ አንዱ ክርስቲያን ከሆነው ወንድሙ ጋር ቢጣላ ጉዳዩን ክርስቲያኖች በፍርድ እንዲያዩለት በማድረግ ፈንታ ለክስ ወደ አሕዛብ የፍርድ ሸንጎ ለመሄድ እንዴት ይደፍራል? 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም1 ከመካከላችሁ አንድ ሰው ከሌላው ጋራ ሙግት ቢኖረው፣ ጕዳዩን በቅዱሳን ፊት በማቅረብ ፈንታ እንዴት ደፍሮ በዐመፀኞች ፊት ለመፋረድ ያቀርባል? 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 ከእናንተ አንዱ ከባልንጀራው ጋር ጥል ቢኖረው በቅዱሳን ፊት በመፋረድ ፋንታ በአሕዛብ ፊት ሊፋረድ እንዴት ይደፍራል? 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 እንግዲህ በሚነቅፉ ሰዎች ዘንድ ልትከራከሩ አትድፈሩ፤ ከጓደኛው ጋር በዐመፀኞች ዘንድ ሊከራከር የሚችል አለን? በደጋጎች ዘንድ አይደለምን? ከባልንጀራው ጋር ክርክር ያለው ቢኖርም በቅዱሳን ዘንድ ይከራከር፤ በሚነቅፉና በዐመፀኞች ዘንድ ግን አይደለም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ከእናንተ አንዱ ከባልንጀራው ጋር ሙግት ቢኖረው በቅዱሳን ፊት በመፋረድ ፋንታ በዓመፀኞች ፊት ሊፋረድ ይደፍራልን? 参见章节 |