Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ቆሮንቶስ 11:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ኧረ ለመሆኑ የምትበሉበትና የምትጠጡበት ቤት የላችሁምን? ወይስ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትንቃላችሁን? ወይስ ምንም የሌላቸውን ችግረኞች ታሳፍራላችሁን? እንግዲህ ምን ልበላችሁ? ስለዚህ ነገር ላመስግናችሁን? ከቶ አላመሰግናችሁም!

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ለመሆኑ የምትበሉበትና የምትጠጡበት ቤት የላችሁምን? ወይስ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን በመናቅ፣ ምንም የሌላቸውን ታሳፍራላችሁን? እንግዲህ ምን ልበላችሁ? በዚህ ነገር ላመስግናችሁን? ፈጽሞ አላመሰግናችሁም!

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ኧረ ለመሆኑ የምትበሉበትና የምትጠጡበት ቤት የላችሁምን? ወይስ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትንቃላችሁን? ወይስ ምንም የሌላቸውን ታሳፍራላችሁን? ምን ልበላችሁ? በዚህ ነገር ላመስግናችሁን? አላመሰግናችሁም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 በውኑ የም​ት​በ​ሉ​በ​ትና የም​ት​ጠ​ጡ​በት ቤት የላ​ች​ሁ​ምን? ወይስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ታስ​ነ​ቅ​ፋ​ላ​ች​ሁን? ነዳ​ያ​ን​ንስ ታሳ​ፍ​ሩ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ች​ሁን? ምን እላ​ለሁ? በዚህ አመ​ሰ​ግ​ና​ች​ኋ​ለ​ሁን? አላ​መ​ሰ​ግ​ና​ች​ሁም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 የምትበሉባቸውና የምትጠጡባቸው ቤቶች የላችሁምን? ወይስ የእግዚአብሔርን ማኅበር ትንቃላችሁን አንዳችም የሌላቸውን ታሳፍራላችሁን? ምን ልበላችሁ? በዚህ ነገር ላመስግናችሁን? አላመሰግናችሁም።

参见章节 复制




1 ቆሮንቶስ 11:22
10 交叉引用  

በድኾች ብታፌዝ የፈጠራቸውን እግዚአብሔርን እንደ ሰደብክ ይቈጠራል፤ በሌላው ሰው ላይ በሚደርሰው መከራ ብትደሰት አንተም ትቀጣለህ።


መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ሾሞአችኋል፤ እንግዲህ ለራሳችሁና ለመንጋው ተጠንቀቁ፤ እግዚአብሔር በገዛ ልጁ ደም የዋጃትን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ።


አይሁድንም ቢሆን፥ አሕዛብንም ቢሆን፥ የእግዚአብሔርንም ቤተ ክርስቲያን ቢሆን፥ ማንንም አታሰናክሉ።


በምትሰበሰቡበት ጊዜ የምታደርጉት ክፉ እንጂ መልካም ነገር ስላልሆነ በዚህ አሁን በምሰጣችሁ ትምህርት አላመሰግናችሁም።


ዘወትር ስለምታስታውሱኝና የሰጠኋችሁንም ትውፊት አጥብቃችሁ ስለ ያዛችሁ፥ አመሰግናችኋለሁ።


መሰብሰባችሁ ለፍርድ እንዳይሆን ከመካከላችሁ የራበው ሰው ቢኖር በቤቱ ይብላ። ስለ ቀረው ነገር እኔ እዚያ ስመጣ ተጨማሪ መመሪያ እሰጣችኋለሁ።


እኔ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ያሳደድኩ ስለ ሆነ ከሐዋርያት ሁሉ ያነስኩና ሐዋርያም ተብዬ ልጠራ የማይገባኝ ነኝ።


ሰው የገዛ ራሱን ቤተሰብ ማስተዳደር የማይችል ከሆነ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ማስተዳደር እንዴት ይችላል?


跟着我们:

广告


广告