Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 9:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ከቆሬ ጐሣ የሻሉም የበኲር ልጅ የሆነው ማቲትያ የመባውን ኅብስት የማዘጋጀት ኀላፊነት ነበረው፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 የቆሬያዊው የሰሎም በኵር ልጅ ሌዋዊው ማቲትያ የቍርባኑን እንጀራ የመጋገር ኀላፊነት ተሰጥቶት ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 የቆሬያዊውም የሰሎም በኩር ሌዋዊው ማቲትያ በምጣድ በሚጋገረው ኅብስት ላይ ሹም ነበረ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 የቆ​ሬ​ያ​ዊ​ውም የሰ​ሎም በኵር ሌዋ​ዊው ማቲ​ትያ ለታ​ላቁ ሊቀ ካህ​ናት በም​ጣድ በሚ​ጋ​ገ​ረው ነገር ላይ ሹም ነበረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 የቆሬያዊውም የሰሎም በኵር ሌዋዊው ማቲትያ በምጣድ በሚጋገረው ነገር ላይ ሹም ነበረ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 9:31
10 交叉引用  

ነገር ግን ወደ ቤቱ እንዲገቡ አጥብቆ ስለ ለመናቸው፥ ከእርሱ ጋር ወደ ቤቱ ገቡ፤ ከዚህም በኋላ ሎጥ እንጀራ ጋግረው መልካም ራት እንዲያዘጋጁ ለአገልጋዮቹ ነገራቸው፤ ራትም በተዘጋጀ ጊዜ እንግዶቹ በሉ።


ለእግዚአብሔር መባ ሆኖ ለሚቀርበው ኅብስትና ዱቄት፥ ያለ እርሾ ለሚጋገረው ቂጣና በወይራ ዘይት ለሚለወሰው ዱቄት ኀላፊዎች ሲሆኑ፥ ለቤተ መቅደስ መባ ሆኖ የሚቀርበውን ሁሉ የሚመዝኑና የሚለኩ እነርሱ ነበሩ፤


በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩ የቤተ መቅደስ ዘበኞች የሚከተሉት ናቸው፦ ሻሉም፥ ዓቁብ፥ ጣልሞን፥ አሒማንና ወንድሞቻቸው፤ የእነርሱም አለቃ ሻሉም ነበር፤


የኤቢያሳፍ የልጅ ልጅ የቆሬ ልጅ ሻሉም የቆሬ ጐሣ አባሎች ከሆኑት ከሌሎች ዘመዶቹ ጋር በመሆን የቀድሞ አባቶቻቸው የእግዚአብሔርን ሰፈር ይጠብቁ በነበረው ዐይነት እግዚአብሔር ወደሚመለክበት ድንኳን የሚያስገባውን በር ይጠብቁ ነበር።


መግቢያ በሮችንና ቅጽር በሮችን ለመጠበቅ የተመረጡ በአጠቃላይ ሁለት መቶ ዐሥራ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ እነርሱም በሚኖሩባቸው መንደሮች መሠረት ተቈጥረው ተመዘገቡ፤ የእነርሱን የቀድሞ አባቶች በዚህ ኀላፊነት የመደቡአቸው ንጉሥ ዳዊትና ነቢዩ ሳሙኤል ነበሩ።


አራቱም ሌዋውያን የዘበኞች አለቆች ሲሆኑ እነርሱም ሙሉ ሥልጣን ያላቸው ነበሩ፤ እንዲሁም በቤተ መቅደሱ ላሉት ክፍሎችና በውስጣቸውም ለሚቀመጡ ዕቃዎች ኀላፊዎች ነበሩ።


መባው በምጣድ የተጋገረ ኅብስት ከሆነ እርሾ ሳይነካው የወይራ ዘይት ተጨምሮበት ከላመ ዱቄት የተዘጋጀ ይሁን፤


መባው በመጥበሻ የተጋገረ ቂጣ ከሆነ የወይራ ዘይት ተጨምሮበት ከተለወሰ የላመ ዱቄት የተዘጋጀ ይሁን።


“ስለ እህል መባ አቀራረብ የተደነገጉት መመሪያዎች እነዚህ ናቸው፦ ትውልዱ ከአሮን ዘር የሆነ ካህን የእህሉን መባ በመሠዊያው ፊት ለፊት ለእግዚአብሔር ያቅርብ፤


በዘይት ተለውሶና በሚገባ ተቀላቅሎ እንደ እህል መሥዋዕት ከተጋገረ በኋላ መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የእህል መባ ሆኖ ይቅረብ፤


跟着我们:

广告


广告