Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 4:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ከቤተሰቡ መካከል እጅግ የተከበረ ያዕቤጽ ተብሎ የሚጠራ አንድ ሰው ነበር፤ እናቱ እርሱን በወለደች ጊዜ ከባድ የምጥ ጣር ደርሶባት ስለ ነበር “ያዕቤጽ” የሚል ስም አወጣችለት፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ያቤጽ ከወንድሞቹ ይልቅ የተከበረ ሰው ነበረ፤ እናቱም “በጣር የወለድሁት” ስትል ስሙን ያቤጽ አለችው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ያቤጽም ከወንድሞቹ ይልቅ የተከበረ ነበረ፤ እናቱም፦ “በጣር ወልጄዋለሁና” ብላ ስሙን፦ ያቤጽ ብላ ጠራችው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ያግ​ቤ​ጽም ከወ​ን​ድ​ሞቹ ይልቅ የተ​ከ​በረ ነበረ፤ እና​ቱም፦ በጣር ወል​ጄ​ዋ​ለ​ሁና ብላ ስሙን፦ ያግ​ቤጽ ብላ ጠራ​ችው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ያቤጽም ከወንድሞቹ ይልቅ የተከበረ ነበረ፤ እናቱም “በጣር ወልጄዋለሁና” ብላ ስሙን “ያቤጽ” ብላ ጠራችው።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 4:9
10 交叉引用  

ሴቲቱንም፥ “በእርግዝናሽ ወራት ጭንቀትሽን፥ በምትወልጂበትም ጊዜ የምጥ ሥቃይሽን አበዛሁ፤ ይህም ሁሉ ሆኖ ፍላጎትሽ ለባልሽ ይሆናል። ለእርሱም ታዛዥ ትሆኚአለሽ” አላት።


ሴኬም፥ የያዕቆብን ልጅ እጅግ ወዶአት ስለ ነበር የተነገረውን ሁሉ ለማድረግ ምንም ጊዜ አልወሰደበትም፤ ከዚህም በላይ በቤተሰቡ ውስጥ እጅግ የተከበረ በመሆኑ የፈለገውን ለማድረግ መብት ነበረው።


እርስዋ ግን ልትሞት ታጣጥር ስለ ነበር ከመሞቷ በፊት ልጅዋን “ቤንኦኒ” አለችው፤ አባቱ ግን “ብንያም” አለው።


ያዕቤጽም “አምላኬ ሆይ፥ ባርከኝ፤ ሰፊ ምድርንም ስጠኝ፤ እጅህ ከእኔ ጋር ይሁን፤ ሥቃይ ሊያስከትልብኝ ከሚችል ከማንኛውም ክፉ ነገር ጠብቀኝ” በማለት ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።


ቆጽም ዓኑብና ጾቤባ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እንዲሁም ቆጽ የሃሩም ልጅ የአሐርሔል ዘሮች ለሆኑት ጐሣዎች የነገድ አባት ነው።


ከዚህ በኋላ ኤፍሬም ከሚስቱ ጋር ግንኙነት አደረገ፤ እርስዋም ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች፤ በቤተሰባቸው ላይ በደረሰው መከራ ምክንያት በሪዓ የሚል ስም አወጣለት።


አባትህና እናትህ በአንተ ደስ ይበላቸው፤ እናትህም በአንተ ሐሤት ታድርግ።


እናንተ በእኔ ፊት የተወደዳችሁ ናችሁ፤ ስለምወዳችሁ ሕይወታችሁን ለማዳን ሕዝቦችንና መንግሥታችን አሳልፌ እሰጣለሁ።


በቤርያ ያሉት አይሁድ በተሰሎንቄ ካሉት ይልቅ ቅን አመለካከት ያላቸው ስለ ነበሩ ቃሉን በታላቅ ደስታ ተቀበሉ፤ የቃሉንም እውነተኛነት ለማረጋገጥ በየቀኑ ቅዱሳት መጻሕፍትን ይመረምሩ ነበር።


እርስዋም በእግዚአብሔር ታቦት መማረክ፥ በዐማትዋና በባልዋ መሞት ምክንያት ክብር ከእስራኤል ተለየ ስትል ልጅዋን ኢካቦድ ብላ ሰየመችው።


跟着我们:

广告


广告