Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 4:41 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመነ መንግሥት ከላይ የተጠቀሱት ሰዎች ወደ ገራር ሄደው በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ድንኳንና ጎጆ ሁሉ አፈራረሱ፤ የካምን ነገዶችና መዑናውያንንም ፈጽመው ፈጁአቸው ለበጎቻቸው ብዙ የግጦሽ ቦታ ስላገኙም ሕዝቡን አባረው ለዘለቄታው እዚያው መኖር ጀመሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 እነዚህ ስማቸው ከላይ የተዘረዘረው ወደዚህ ቦታ የመጡት በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን ነበረ፤ እነርሱም በድንኳኖቻቸው ውስጥ በነበሩት በካም ወገኖችና በምዑናውያን ላይ አደጋ በመጣል ፈጽመው አጠፏቸው፤ ይህም እስከ ዛሬ ድረስ በግልጽ ይታያል። ለመንጎቻቸው በቂ የግጦሽ ቦታ ስላገኙም፣ በዚያ መኖር ጀመሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 እነዚህም በስማቸው የተጻፉ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን መጥተው ድንኳኖቻቸውንና በዚያ የተገኙትን ምዑናውያንን መቱ፥ እስከ ዛሬም ድረስ ፈጽመው አጠፉአቸው፤ በዚያም ለመንጎቻቸው መሰማሪያ ነበረና በስፍራቸው ተቀመጡ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 በስ​ማ​ቸው የተ​ጻፉ እነ​ዚ​ህም በይ​ሁዳ ንጉሥ በሕ​ዝ​ቅ​ያስ ዘመን መጥ​ተው ድን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንና በዚያ የተ​ገ​ኙ​ትን ምዑ​ና​ው​ያ​ንን መቱ፥ እስከ ዛሬም ድረስ ፈጽ​መው አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ በዚ​ያም ለመ​ን​ጎ​ቻ​ቸው መሰ​ማ​ሪያ ነበ​ርና በስ​ፍ​ራ​ቸው ተቀ​መጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 እነዚህም በስማቸው የተጻፉ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን መጥተው ድንኳኖቻቸውንና በዚያ የተገኙትን ምዑናውያንን መቱ፤ እስከ ዛሬም ድረስ ፈጽመው አጠፉአቸው፤ በዚያም ለመንጎቻቸው መሰማርያ ነበረና በስፍራቸው ተቀመጡ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 4:41
13 交叉引用  

አካዝ፥ ሕዝቅያስ፥ ምናሴ፥


በአካባቢያቸው በሚገኙ መንደሮች ይኖሩ ነበር፤ ይህም እነርሱ የሚኖሩበት ስፍራ እስከ ባዕላት ከተማ ይዘልቅ ነበር። እንግዲህ የስምዖን ዘሮች ስለ ቤተሰቦቻቸውና ስለሚኖሩባቸው ስፍራዎች መዝግበው ያቈዩት ጽሑፍ ይህ ነበር።


ጦርነቱ እግዚአብሔር የፈቀደው ስለ ነበረ፥ ከጠላት ወገን ብዙ ሰዎችን ገደሉ፤ እነርሱም ራሳቸው ተማርከው እስከ ተወሰዱበት ጊዜ ድረስ በምድሪቱ ላይ መኖራቸውን ቀጠሉ።


እንዲሁም በአንዳንድ እረኞች ሰፈር ላይ አደጋ በመጣል ብዙ በጎችን፥ ፍየሎችንና ግመሎችን ማረኩ፤ ከዚህም በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው ሄዱ።


ከዚህ በኋላ የዐሞንና የሞአብ ሠራዊት ከእነርሱም ጋር የጦር ቃል ኪዳን ጓደኞቻቸው የሆኑት መዑናውያን ኢዮሣፍጥን ለመዋጋት መጡ፤


ፍልስጥኤማውያንን፥ በጒርባዓል ይኖሩ የነበሩትን ዐረቦችና መዑናውያንን ድል እንዲያደርግ እግዚአብሔር ረዳው።


ስለዚህም በኤዶም ሕዝብ ላይ ያቀድኩትንና በቴማን ከተማ ሕዝብ ላይ ላደርግ የፈለግኹትን ስሙ፤ ልጆቻቸው እንኳ እንደ በግ ግልገሎች እየተጐተቱ ይወሰዳሉ፤ በእነርሱም ምክንያት የሚያያቸው ሁሉ ይደነግጣል።


እርሱ የሰውን ዘር ሁሉ ከአንድ ሰው ፈጠረ፤ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩም አደረገ፤ የተወሰኑ ዘመኖችንና የሚኖሩባቸውንም ቦታዎች መደበላቸው።


跟着我们:

广告


广告