Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 29:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ከዚህ በኋላ የጐሣ አለቆች፥ የየነገዱ መሪዎች፥ የሺህ አለቆችና የመቶ አለቆች የመንግሥት ባለሥልጣኖች በፈቃዳቸው ስጦታ ሰጡ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ከዚያም የቤተ ሰብ መሪዎች፣ የነገዱ የእስራኤል ሹማምት፣ የሻለቆችና የመቶ አለቆች እንዲሁም በንጉሡ ሥራ ላይ የተመደቡ ሹማምት በፈቃዳቸው ሰጡ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የአባቶችም ቤቶች አለቆች፥ የእስራኤልም ነገዶች አለቆች፥ ሻለቆችም፥ የመቶ አለቆችም፥ በንጉሡም ሥራ ላይ የተሾሙት በፈቃዳቸው አቀረቡ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የአ​ባ​ቶ​ችም ቤቶች አለ​ቆች፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አለ​ቆች፥ ሻለ​ቆ​ችም፥ የመቶ አለ​ቆ​ችም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ሥራ የተ​ሾ​ሙና የን​ጉሡ ግን​በ​ኞች በፈ​ቃ​ዳ​ቸው አቀ​ረቡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የአባቶችም ቤቶች አለቆች፥ የእስራኤልም ነገዶች አለቆች፥ ሻለቆችም፥ የመቶ አለቆችም፥ በንጉሡም ሥራ ላይ የተሾሙት በፈቃዳቸው አቀረቡ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 29:6
9 交叉引用  

እያንዳንዱ ካህን ከሚያገለግላቸው ሰዎች የሚገኘውን የገንዘብ መባ ሁሉ በጥንቃቄ የመጠበቅ ኀላፊነት ተሰጠው፤ ገንዘቡንም እንዳስፈላጊነቱ ለቤተ መቅደሱ ጥገና አገልግሎት እንዲያውሉት ነገራቸው።


የቤተ መንግሥት ንብረት ኀላፊዎች የሆኑት ሰዎች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፦ የቤተ መንግሥት ዕቃ ግምጃ ቤት ኀላፊ የዐዲኤል ልጅ ዓዝማዌት በየገጠሩ፥ በየከተማው፥ በየመንደሩ በየምሽጉ የሚገኙ የመንግሥት ዕቃ ግምጃ ቤት ኀላፊ፦ የዑዚያ ልጅ ዮናታን የግብርና ሥራ ኀላፊ፦ የከሉብ ልጅ ዔዝሪ የወይን ተክል ቦታዎች ኀላፊ የራማ ተወላጅ የሆነው ሺምዒ የወይን ጠጅ ዕቃ ግምጃ ቤት ኀላፊ፦ የሸፋም ተወላጅ የሆነው ዛብዲ በደቡባዊ ኰረብቶች የሚገኙት የወይራና የወርካ ዛፎች ኀላፊ፦ የጌዴር ተወላጅ የሆነው ባዓልሐናን የወይራ ዘይት ግምጃ ቤት ኀላፊ ኢዮአስ በሳሮን ሜዳ የሚገኙት የቀንድ ከብቶች ኀላፊ የሳሮን ተወላጅ የሆነው ሺጥራይ በሸለቆዎች የሚገኙ የቀንድ ከብቶች አስተዳዳሪ፦ የዓድላይ ልጅ ሻፋጥ የግመሎች ኀላፊ፦ እስማኤላዊው ኦቢል የአህዮች ኀላፊ፦ የሜሮኖት ተወላጅ የሆነው ዬሕድያ የበጎችና የፍየሎች ኀላፊ፦ ሀግራዊው ያዚዝ።


ንጉሥ ዳዊት የእስራኤል ባለ ሥልጣኖች በሙሉ ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው እንዲሰበሰቡ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ ስለዚህ የየነገዱ መሪዎች፥ የመንግሥቱን ሥራ የሚያካሂዱ ባለሥልጣኖች የሻአለቆችና የመቶ አለቆች፥ የንጉሡንና የወንዶች ልጆቹን ንብረትና የቀንድ ከብት ተቈጣጣሪዎች እንዲሁም የቤተ መንግሥት ባለሟሎች፥ ዝነኞችና ታዋቂ የሆኑ ጀግኖች ሰዎች በሙሉ በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ።


የእጅ ጥበብ ዐዋቂዎች ለሚሠሩአቸው ዕቃዎች መሥሪያ የሚውል ሰጥቼአለሁ፤ ከእናንተስ መካከል በፈቃዱ ለእግዚአብሔር በልግሥና የሚሰጥ ሌላ ማን አለ?”


የንጉሡ ባለሟሎች የሆኑ ባለሥልጣኖችም መሥዋዕት ሆነው የሚቀርቡ እንስሶችን በገዛ ፈቃዳቸው ለምእመናን፥ ለካህናትና ለሌዋውያን ሰጡ፤ የቤተ መቅደሱ አለቆች የሆኑት ሊቃነ ካህናቱ ሒልቂያ፥ ዘካርያስና ይሒኤልም የፋሲካ መሥዋዕት ሆነው የሚቀርቡ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ የበግና የፍየል ጠቦቶችንና ሦስት መቶ በሬዎችን ለካህናት ሰጡ፤


ከዚህም ሁሉ ጋር አንተ ራስህ ከባቢሎን ምድር የሰበሰብከውን ወርቅና ብር፥ የእስራኤል ሕዝብና ካህናታቸውም ጭምር በኢየሩሳሌም በተሠራው የአምላካቸው ቤተ መቅደስ እንዲቀርብላቸው የሚፈልጉትን መባ ሁሉ ይዘህ ሂድ።


ስለዚህ እግዚአብሔር የሚወደው በደስታ የሚሰጠውን ሰው ስለ ሆነ እያንዳንዱ ለመስጠት የፈለገውን በልቡ ፈቅዶ በደስታ ይስጥ እንጂ እያመነታ ወይም በግዴታ አይስጥ።


跟着我们:

广告


广告