Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 29:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ብዙ ሀብትና ክብር ካገኘም በኋላ በዕድሜ እጅግ ሸምግሎ ሞተ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ሰሎሞን ነገሠ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ብዙ ዘመን ባለጠግነትና ክብር ሳይጐድልበት ዕድሜ ጠግቦ ሞተ፤ ልጁ ሰሎሞንም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ዕድሜም፥ ባለጠግነትም፥ ክብርም ጠግቦ በመልካም ሽምግልና ሞተ፤ ልጁም ሰሎሞን በእርሱ ፋንታ ነገሠ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ዕድ​ሜም፥ ባለ​ጠ​ግ​ነ​ትም፥ ክብ​ርም ጠግቦ በመ​ል​ካም ሽም​ግ​ልና ሞተ፤ ልጁም ሰሎ​ሞን በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ዕድሜም፥ ባለጠግነትም፥ ክብርም ጠግቦ በመልካም ሽምግልና ሞተ፤ ልጁም ሰሎሞን በእርሱ ፋንታ ነገሠ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 29:28
13 交叉引用  

አንተ ግን ብዙ ዘመን ኖረህ በሰላም ትሞታለህ፤ በሰላምም ትቀበራለህ።


በዚህም ዐይነት አብርሃም በቂ ዕድሜ አግኝቶ ካረጀ በኋላ ሞተ፤


ዕድሜ ጠግቦ ካረጀ በኋላ ሞተ፤ ልጆቹም ዔሳውና ያዕቆብ ቀበሩት።


ልጅሽ ሰሎሞን በእኔ እግር ተተክቶ እንደሚነግሥ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ከዚህ በፊት የገባሁልሽን ቃል በዛሬው ዕለት የምፈጽም መሆኔን አረጋግጥልሻለሁ።”


ዳዊት በጣም በሸመገለ ጊዜ ልጁን ሰሎሞንን በእስራኤል ላይ አነገሠው።


ለእኔም ብዙ ወንዶች ልጆችን ሰጠኝ፤ ነገር ግን የሚቀጥለው የእስራኤል ንጉሥ ይሆን ዘንድ የመረጠው ልጄን ሰሎሞንን ነው።”


ሰሎሞንም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “አንተ ለአባቴ ለዳዊት ታላቅ ፍቅርህን ባለማቋረጥ አሳይተኸዋል፤ አሁንም እኔ በአባቴ እግር ተተክቼ እንድነግሥ አድርገሃል፤


ንጉሥ ሕዝቅያስ እጅግ በለጸገ፤ ሕዝቡም ሁሉ አከበሩት፤ ወርቁን፥ ብሩን፥ የከበረ ዕንቊውን፥ ቅመማ ቅመሙን፥ ጋሻዎቹንና ሌሎቹንም ውድ የሆኑ ዕቃዎቹን የሚያኖርባቸው ዕቃ ግምጃ ቤቶችን ሠራ፤


ከዚህም ሁሉ ሌላ እግዚአብሔር ብዙ የቀንድ ከብትና የበግ መንጋ እንዲሁም ሌላ እጅግ የበዛ ሀብት ስለ ሰጠው፥ ብዙ ከተሞችን ሠራ፤


የስንዴ እሸት እስኪጐመራ በማሳ ላይ እንደሚቈይ አንተም በዕድሜ እስከምትሸመግል ትኖራለህ።


እነዚህ ምሳሌዎች የዳዊት ልጅ የሆነው፥ የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን የተናገራቸው ናቸው።


ሽበት የክብር ዘውድ ነው። የሚገኘውም በተቀደሰ አኗኗር ነው።


ነገር ግን ዳዊት በሕይወቱ ዘመን አገልግሎቱን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ከፈጸመ በኋላ ሞቶአል፤ ከአባቶቹም ጋር ተቀብሮአል፤ መበስበስም ደርሶበታል።


跟着我们:

广告


广告