Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 28:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ለእኔም ብዙ ወንዶች ልጆችን ሰጠኝ፤ ነገር ግን የሚቀጥለው የእስራኤል ንጉሥ ይሆን ዘንድ የመረጠው ልጄን ሰሎሞንን ነው።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እግዚአብሔር ብዙ ልጆች ሰጥቶኛል፤ ከወንዶቹ ልጆቼ ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋን ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ሁሉ ላይ እንዲነግሥ ደግሞ ልጄን ሰሎሞንን መርጦታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ጌታም ብዙ ልጆች ሰጥቶኛልና ከልጆቼ ሁሉ በጌታ መንግሥት ዙፋን ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ላይ እንዲነግሥ ልጄን ሰሎሞንን መርጦታል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብዙ ልጆች ሰጥ​ቶ​ኛ​ልና ከል​ጆቼ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ዙፋን ላይ ተቀ​ምጦ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ይነ​ግሥ ዘንድ ልጄን ሰሎ​ሞ​ንን መር​ጦ​ታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እግዚአብሔርም ብዙ ልጆች ሰጥቶኛልና ከልጆቼ ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋን ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ላይ ይነግሥ ዘንድ ልጄን ሰሎሞንን መርጦታል።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 28:5
19 交叉引用  

ወደ ንጉሥ ዳዊት ገብተሽ ‘ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ነግሦ በዙፋኔ ይቀመጣል’ ብለህ ለአገልጋይህ በመሐላ ቃል ገብተህልኝ አልነበረምን? ታዲያ፥ አሁን አዶንያስ እንዴት ሊነግሥ ቻለ? ብለሽ ንገሪው”።


ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ከአንተ በኋላ የሚነግሠው ማን መሆኑን እንድታስታውቀው በመጠባበቅ ላይ ነው፤


ልጅሽ ሰሎሞን በእኔ እግር ተተክቶ እንደሚነግሥ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ከዚህ በፊት የገባሁልሽን ቃል በዛሬው ዕለት የምፈጽም መሆኔን አረጋግጥልሻለሁ።”


በዙፋኔ ላይ ለመቀመጥ ወደዚህ ተመልሶ በሚመጣበት ጊዜ አጅባችሁት ኑ፤ የእስራኤልና የይሁዳ ንጉሥ ገዢ እንዲሆን የመረጥኩት ስለ ሆነ እርሱ ከእኔ በኋላ ይነግሣል።”


አዶንያስም እንዲህ አላት፦ “ንጉሥ መሆን የሚገባኝ እኔ እንደ ነበርኩና ይህንንም በእስራኤል ምድር የሚኖር ሁሉ በተስፋ ይጠባበቅ እንደ ነበር አንቺ ራስሽ ታውቂያለሽ፤ ነገር ግን ጉዳዩ ከእግዚአብሔር ስለ ተወሰነ ለእኔ መሰጠት የሚገባው መንግሥት ተላልፎ ለወንድሜ ሆኖአል።


“እነሆ እግዚአብሔር የሰጠውን የተስፋ ቃል ጠብቆአል፤ ስለዚህም እኔ በአባቴ እግር ተተክቼ የእስራኤል ንጉሥ ሆኜአለሁ፤ ለእስራኤል አምላክ ቤተ መቅደስንም ሠርቼአለሁ፤


በሕዝቤና በመንግሥቴ ላይ ለዘለዓለም እሾመዋለሁ፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ አይኖረውም።’ ”


ዳዊት በጣም በሸመገለ ጊዜ ልጁን ሰሎሞንን በእስራኤል ላይ አነገሠው።


ንጉሥ ዳዊት ለመላው ጉባኤ እንዲህ ሲል አስታወቀ፤ “እነሆ እግዚአብሔር የመረጠው ልጄ ሰሎሞን ገና ወጣትና የሥራ ልምድ የሌለው ነው፤ ይህ የሚሠራው ቤት፥ ቤተ መንግሥት ሳይሆን እግዚአብሔር አምላካችን የሚመለክበት ቤተ መቅደስ ስለ ሆነ መከናወን ያለበት ሥራ እጅግ ከባድ ነው።


በዚህ ዐይነት ሰሎሞን በአባቱ እግር ተተክቶ እግዚአብሔር ባጸናው ዙፋን ላይ ተቀመጠ፤ እርሱም ሁሉ ነገር የተሳካለት ንጉሥ ሆነ፤ መላውም የእስራኤል ሕዝብ ታዘዙለት፤


ብዙ ሀብትና ክብር ካገኘም በኋላ በዕድሜ እጅግ ሸምግሎ ሞተ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ሰሎሞን ነገሠ፤


ንጉሥ ሆነህ በእርሱ ስም ትገዛ ዘንድ አንተን መርጦ የእስራኤል ንጉሥ ለማድረግ መልካም ፈቃዱ ስለ ሆነ አምላክህ እግዚአብሔር ይመስገን! በፍቅሩም እስራኤል ለዘለዓለም ጸንቶ እንዲኖር ስለ ፈለገ ሕግና ፍትሕ ጸንቶ እንዲኖር ታደርግ ዘንድ አንተን መርጦ ንጉሥ አድርጎሃል።”


እግዚአብሔር አምላክህ የሚመርጥልህን ንጉሥ ልታነግሥ ትችላለህ፤ በአንተም ላይ የምታነግሠው ንጉሥ ከወገንህ መካከል ይሁን፥ ከወገንህ ያልሆነውን የውጪ አገር ሰው ልታነግሥ አይገባህም።


跟着我们:

广告


广告