Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 28:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ለተለያዩ የአገልግሎት ዐይነቶች መጠቀሚያ የሚሆኑትን ዕቃዎች መሥሪያ እንዲሆኑ የብሩንና የወርቁን መጠን በሚዛን ወሰነ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ለልዩ ልዩ አገልግሎት የሚውሉትን የወርቅ ዕቃዎች ሁሉ መጠን፣ ለልዩ ልዩ አገልግሎት የሚውሉትን የብር ዕቃዎች ሁሉ መጠን አሳወቀው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ለአገልግሎት ሁሉ ለሚሆነውም ለወርቁ ዕቃ ወርቁን በሚዛን ሰጠው፤ ለአገልግሎት ሁሉ ለሚሆነውም ለብር ዕቃ ሁሉ ብሩን በሚዛን ሰጠው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ለወ​ርቁ ዕቃ ወር​ቁን በሚ​ዛን ሰጠው፤ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት ሁሉ ለሚ​ሆ​ነ​ውም ለብር ዕቃ ሁሉ ብሩን በሚ​ዛን ሰጠው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ለአገልግሎት ሁሉ ለሚሆነውም ለወርቁ ዕቃ ወርቁን በሚዛን ሰጠው፤ ለአገልግሎት ሁሉ ለሚሆነውም ለብር ዕቃ ሁሉ ብሩን በሚዛን ሰጠው፤

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 28:14
5 交叉引用  

እንዲሁም ዳዊት ስለ ካህናትና ሌዋውያን የተለያየ የሥራ ድርሻ፥ በቤተ መቅደሱ ስለሚከናወኑት ተግባሮችና እግዚአብሔርን ለማምለክ አገልግሎት መጠቀሚያ ለሆኑት ዕቃዎች ለሚደረገው እንክብካቤ ዕቅድ ለሰሎሞን ሰጠው።


ለያንዳንዱ መቅረዝና መብራት የሚሆን ወርቅ፥ እንዲሁም ለመቅረዙና ለመብራቱ የሚሆን ብር መዝኖ ሰጠው።


የምችለውን ያኽል፥ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሥራ የሚሆኑትን ዕቃዎች ወርቅ ለወርቅ ሥራ፥ ብር ለብር ሥራ፥ ነሐስ ለነሐስ ሥራ፥ ብረት ለብረት ሥራ፥ እንጨት ለእንጨት ሥራ መርግድና የተለያዩ ቀለማት ያላቸው በፈርጥ የሚገቡ ድንጋዮች፥ የከበረ ድንጋይና በየዐይነቱ ብዙ ዕብነ በረድ አዘጋጅቼአለሁ።


ሰሎሞን በተዘጋጀው ዕቅድ መሠረት ዐሥር መቅረዞችን ከወርቅ አሠርቶ በቤተ መቅደሱ ዋና ክፍል ውስጥ አምስቱን በሰሜን፥ አምስቱን በደቡብ በኩል አኖራቸው።


ከዚህም በኋላ በአራተኛው ቀን ወደ ቤተ መቅደስ ሄድን፤ ብሩን፥ ወርቁንና ንዋያተ ቅድሳቱንም ሁሉ መዝነን ለኡሪያ ልጅ ለካህኑ ለመሬሞት አስረከብነው፤ የፊንሐስ ልጅ አልዓዛርና እንዲሁም ሌዋውያኑ ዮዛባድ ተብሎ የሚጠራው የኢያሱ ልጅና ኖዓዲያ ተብሎ የሚጠራው የቢኑይ ልጅ ከእርሱ ጋር አብረው ነበሩ።


跟着我们:

广告


广告