የቤተ መንግሥት ንብረት ኀላፊዎች የሆኑት ሰዎች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፦ የቤተ መንግሥት ዕቃ ግምጃ ቤት ኀላፊ የዐዲኤል ልጅ ዓዝማዌት በየገጠሩ፥ በየከተማው፥ በየመንደሩ በየምሽጉ የሚገኙ የመንግሥት ዕቃ ግምጃ ቤት ኀላፊ፦ የዑዚያ ልጅ ዮናታን የግብርና ሥራ ኀላፊ፦ የከሉብ ልጅ ዔዝሪ የወይን ተክል ቦታዎች ኀላፊ የራማ ተወላጅ የሆነው ሺምዒ የወይን ጠጅ ዕቃ ግምጃ ቤት ኀላፊ፦ የሸፋም ተወላጅ የሆነው ዛብዲ በደቡባዊ ኰረብቶች የሚገኙት የወይራና የወርካ ዛፎች ኀላፊ፦ የጌዴር ተወላጅ የሆነው ባዓልሐናን የወይራ ዘይት ግምጃ ቤት ኀላፊ ኢዮአስ በሳሮን ሜዳ የሚገኙት የቀንድ ከብቶች ኀላፊ የሳሮን ተወላጅ የሆነው ሺጥራይ በሸለቆዎች የሚገኙ የቀንድ ከብቶች አስተዳዳሪ፦ የዓድላይ ልጅ ሻፋጥ የግመሎች ኀላፊ፦ እስማኤላዊው ኦቢል የአህዮች ኀላፊ፦ የሜሮኖት ተወላጅ የሆነው ዬሕድያ የበጎችና የፍየሎች ኀላፊ፦ ሀግራዊው ያዚዝ።