1 ዜና መዋዕል 27:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 እግዚአብሔር “የእስራኤልን ሕዝብ እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ” ሲል በሰጠው የተስፋ ቃል መሠረት ንጉሥ ዳዊት ዕድሜአቸው ከኻያ ዓመት በታች የሆኑትን በሕዝብ ቈጠራ ውስጥ አላስገባቸውም ነበር፤ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም23 እግዚአብሔር እስራኤልን እንደ ሰማይ ከዋክብት እንደሚያበዛቸው ተስፋ ሰጥቶ ስለ ነበር፣ ዳዊት ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያ በታች የሆነውን አልቈጠረም ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 ጌታ ግን እስራኤልን እንደ ሰማይ ከዋክብት ለማብዛት ተናግሮ ነበርና ዳዊት ከሀያ ዓመት በታች የነበሩትን አልቈጠረም። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 ነገር ግን እግዚአብሔር ሕዝቡ እስራኤልን እንደ ሰማይ ከዋክብት ያበዛ ዘንድ ተናግሮ ነበርና ዳዊት ከሃያ ዓመት በታች የነበሩትን አልቈጠረም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 እግዚአብሔር ግን እስራኤልን እንደ ሰማይ ከዋክብት ያበዛ ዘንድ ተናግሮ ነበርና ዳዊት ከሃያ ዓመት በታች የነበሩትን አልቈጠረም። 参见章节 |