Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 26:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ሸሎሚትና ዘመዶቹ ንጉሥ ዳዊት የቤተሰብ አለቆች፥ የጐሣ ቡድን መሪዎችና የጦር መኰንኖች ለእግዚአብሔር የተለዩ አድርገው ላቀረቡአቸው ስጦታዎች ኀላፊዎች ነበሩ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ሰሎሚትና የሥጋ ዘመዶቹ ንጉሥ ዳዊት፣ የቤተ ሰቡ ኀላፊዎች፣ የሻለቆችና የመቶ አለቆች እንዲሁም ሌሎች የሰራዊቱ አዛዦች ቀድሰው ላቀረቧቸው ንዋያተ ቅድሳት ኀላፊዎች ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ይህ ሰሎሚትና ወንድሞቹ ንጉሡ ዳዊትና የአባቶች ቤቶች አለቆች፥ ሻለቆችና የመቶ አለቆች የሠራዊቱም አዛዦች፥ በቀደሱት በንዋየ ቅድሳቱ ቤተ መዛግብት ሁሉ ላይ ተሾመው ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ይህ ሰሎ​ሚ​ትና ወን​ድ​ሞቹ፥ ንጉሡ ዳዊ​ትና የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች፥ ሻለ​ቆ​ችና የመቶ አለ​ቆች፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለ​ቆች፥ በቀ​ደ​ሱት በን​ዋየ ቅድ​ሳቱ ቤተ መዛ​ግ​ብት ሁሉ ላይ ተሹ​መው ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ይህ ሰሎሚትና ወንድሞቹ ንጉሡ ዳዊትና የአባቶች ቤቶች አለቆች፥ ሻለቆችና የመቶ አለቆች የሠራዊቱም አለቆች፥ በቀደሱት በንዋየ ቅድሳቱ ቤተ መዛግብት ሁሉ ላይ ተሾመው ነበር።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 26:26
13 交叉引用  

ንጉሥ ዳዊትም ድል ካደረጋቸው ከኤዶም፥ ከሞአብ፥ ከዐሞን፥ ከፍልስጥኤምና ከዐማሌቅ ከወሰደው ብርና ወርቅ፥ እንዲሁም ከሀዳድዔዜር ከወሰደው ምርኮ ጋር እነዚህንም ደግሞ ለእግዚአብሔር የተለዩ አደረገ።


ንጉሥ ዳዊትም እነርሱን ወስዶ ከኤዶም፥ ከሞአብ፥ ከዐሞን፥ ከፍልስጥኤምና ከዐማሌቅ ሕዝቦች ማርኮ ካመጣቸው ከወርቅ፥ ከብርና ከነሐስ ከተሠሩ ዕቃዎች ጋር ለአምልኮ ሥነ ሥርዓት መገልገያ እንዲሆኑ አደረጋቸው።


ስለ ቤተ መቅደሱ ሥራ የሆነ እንደሆን፥ በበኩሌ ለሕንጻ ሥራ የሚውል ሦስት ሺህ አራት መቶ ቶን ወርቅና ከሠላሳ አራት ሺህ ቶን በላይ የሚሆን ብር አከማችቼልሃለሁ፤ በተጨማሪም ስፍር ቊጥር የሌለው ነሐስና ብረት አዘጋጅቼልሃለሁ፤ እንዲሁም እንጨትና ድንጋይ አዘጋጅቼልሃለሁ፤ ይሁን እንጂ አንተም በተጨማሪ ማግኘት አለብህ፤


እርሱም በጌርሾም ወንድም በኤሊዔዘር በኩል ለሸሎሚት የሥጋ ዝምድና ነበረው፤ ኤሊዔዘር ረሐብያን ወለደ፤ ረሐብያም ይሻዕያን ወለደ፤ ይሻዕያ ዮራምን ወለደ፤ ዮራምም ዚክሪን ወለደ፤ ዚክሪም ሼሎሚትን ወለደ፤


እነዚህ ኀላፊዎችም በጦርነት ጊዜ ከተገኘው ምርኮ ጥቂቱን ወስደው ለቤተ መቅደሱ ሥራ የተለየ እንዲሆን ያደርጉ ነበር።


በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያለውን አገልግሎት እንዲፈጽሙ ካህናትና ሌዋውያን ተመድበዋል፤ ልዩ ልዩ ችሎታ ያላቸው ሠራተኞች ይረዱሃል፤ ሕዝቡና መሪዎቻቸው ሁሉ ለአንተ ይታዘዛሉ።”


በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩት ሌዋውያን የሚከተሉት ናቸው፦ የሐሹብ ልጅ ሸማዕያ፤ የእርሱም የቀድሞ አባቶች ከመራሪ ጐሣዎች የነበሩት ዓዝሪቃምና ሐሻብያ ናቸው። ባቅባቃር፥ ሔሬሽና ጋላል፤ የሚካ ልጅ ማታንያ፤ የእርሱም የቀድሞ አባቶች ዚክሪና አሳፍ ናቸው። የሸማዕያ ልጅ አብድዩ የእርሱም የቀድሞ አባቶች ጋላልና ይዱታን ናቸው። የነጦፋ ከተማ ይዞታ በነበረው ግዛት ይኖር በነበረው የኤልቃና የልጅ ልጅ የአሳ ልጅ ቤሬክያ።


ሌዋውያንና የይሁዳ ሕዝብ ካህኑ ዮዳሄ የሰጣቸውን መመሪያ ሁሉ ፈጸሙ፤ ዮዳሄም አገልግሎታቸውን ፈጽመው በሰንበት ቀን ከሥራ ነጻ መሆን የሚገባቸው ሌዋውያን አላሰናበታቸውም ነበር፤ ስለዚህ ለዘብ ጥበቃ የሚሰማሩትና ከዘብ ጥበቃ ነጻ የሆኑት እዚያው ስለ ነበሩ የጦር መኰንኖቹ በቂ ሰዎች ነበሩአቸው፤


ንጉሥ ሕዝቅያስ የካህናትንና የሌዋውያንን ሥርዓት እንደገና አቋቋመ፤ በዚህም ጉባኤ ውስጥ እያንዳንዱ ካህንና እያንዳንዱ ሌዋዊ የተለየ የሥራ ምድብ ነበረው፤ ይህም የሥራ ምድብ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕትን ማቅረብን፥ በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሚከናወነው የአምልኮ ሥነ ሥርዓት መሳተፍን፥ በሌሎቹም በቤተ መቅደሱ ልዩ ልዩ ክፍሎች ምስጋናና ውዳሴ ማቅረብን የሚያጠቃልል ነበር፤


የይሁዳም ሕዝብ ተደስቶ የነበረው እነርሱ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት መፈጸም የሚገባውን ደንብና የማንጻት ሥርዓት በማከናወናቸው ነበር፥ የቤተ መቅደሱ መዘምራንና የቤተ መቅደሱ ዘብ ጠባቂዎችም ዳዊትና ልጁ ሰሎሞን በመደቡት ሥርዓት መሠረት የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት ፈጸሙ።


跟着我们:

广告


广告