Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 25:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9-31 የመጀመሪያው ዕጣ ከአሳፍ ወገን ለዮሴፍ ወጣ፤ እርሱም፥ ልጆቹም፥ ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ሁለተኛው ለገዳልያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ሦስተኛ ለዛኩር ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። አራተኛው ለይጽሪ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፥ አምስተኛ ለነታንያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ስድስተኛ ለቡቅያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ሰባተኛ ለአሳርኤላ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ስምንተኛው ለያሻዕያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ዘጠነኛው ለማታንያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ዐሥረኛው ለሺምዒ ወጣ፤ እርሱም፥ ልጆቹም፥ ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ዐሥራ አንደኛው ለዓዛርኤል ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ዐሥራ ሁለተኛው ለሐሻብያ ወጣ፥ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ዐሥራ ሦስተኛው ለሹባኤል ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ዐሥራ አራተኛ ለማቲትያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ዐሥራ አምስተኛው ለያሪሞት ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ዐሥራ ስድስተኛው ለሐናንያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ዐሥራ ሰባተኛው ለዮሽበቃሽ ወጣ፥ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ዐሥራ ስምንተኛው ለሐናኒ ወጣ፥ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ዐሥራ ዘጠነኛ ለማሎቲ ወጣ፥ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ኻያኛ ለኤሊአታ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ኻያ አንደኛ ለሆቲር ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ኻያ ሁለተኛ ለጊደልቲ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ኻያ ሦስተኛ ለማሕዚኦት ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ኻያ አራተኛ ለሮሚምቲዔዜር ወጣ፤ እርሱም ልጆቹም፥ ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የመጀመሪያው ዕጣ ከአሳፍ ወገን ለሆነው ለዮሴፍ ወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12 ሁለተኛው ለጎዶልያስ ወጣ፤ እርሱን ጨምሮ ለቤተ ዘመዶቹና ለወንዶች ልጆቹ፤ ቍጥራቸውም 12

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 የፊተኛው ዕጣ ከአሳፍ ወገን ለነበረው ለዮሴፍ ወጣ፤ ሁለተኛው ለጎልዶያስ ወጣ፤ እርሱ ወንድሞቹም ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ዕጣ ለአ​ሳፍ ወገን ለዮ​ሴፍ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹና ለል​ጆቹ ለዐ​ሥራ ሁለቱ ደረ​ሳ​ቸው፤ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ዕጣ ለጎ​ዶ​ል​ያስ ለል​ጆ​ቹና ለወ​ን​ድ​ሞቹ ለዐ​ሥራ ሁለቱ ደረ​ሳ​ቸው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የፊተኛው ዕጣ ከአሳፍ ወገን ለነበረው ለዮሴፍ ወጣ፤ ሁለተኛው ለጎልዶያስ ወጣ፤ እርሱ ወንድሞቹም ልጆቹን አሥራ ሁለት ነበሩ፤

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 25:9
4 交叉引用  

ንጉሥ ዳዊትና የሌዋውያን አለቆች የአሳፍን፥ የሔማንና የይዱቱን ልጆች መንፈስ ቅዱስ ያቀበላቸውን መዝሙር በመሰንቆ፥ በበገናና በጸናጽል እየታጀቡ እንዲዘምሩ ለዩአቸው። ለዚህ አገልግሎት የተመደቡት ሰዎች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፦


የሥራ ምድባቸውን ለመወሰን ወጣት ሆነ ሽማግሌ፥ አስተማሪም ሆነ ተማሪ ለማንም ልዩነት ሳይደረግ ዕጣ ይጣጣሉ ነበር።


跟着我们:

广告


广告