1 ዜና መዋዕል 25:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 የሥራ ምድባቸውን ለመወሰን ወጣት ሆነ ሽማግሌ፥ አስተማሪም ሆነ ተማሪ ለማንም ልዩነት ሳይደረግ ዕጣ ይጣጣሉ ነበር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም8 የሥራ ድርሻቸውንም ለመወሰን ወጣት፣ ሽማግሌ፣ መምህርም ሆነ ደቀ መዝሙር ሳይባል እኩል ዕጣ ተጣጣሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 ታናሹ እንደ ታላቁ፥ አስተማሪው እንደ ተማሪው፥ ሁሉም በተመሳሳይ መልኩ፥ ለሰሞናቸው ዕጣ ተጣጣሉ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 ሁሉም ተካክለው፥ ታናሹም ታላቁም፥ ለሰሞናቸው ዕጣ ተጣጣሉ እነርሱም ፍጹማንና የተማሩ ነበሩ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 ሁሉም ተካክለው፥ ታናሹ እንደ ታላቁ፥ አስተማሪው እንደ ተማሪው፥ ለሰሞናቸው ዕጣ ተጣጣሉ። 参见章节 |
የመጀመሪያው ዕጣ ከአሳፍ ወገን ለዮሴፍ ወጣ፤ እርሱም፥ ልጆቹም፥ ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ሁለተኛው ለገዳልያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ሦስተኛ ለዛኩር ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። አራተኛው ለይጽሪ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፥ አምስተኛ ለነታንያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ስድስተኛ ለቡቅያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ሰባተኛ ለአሳርኤላ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ስምንተኛው ለያሻዕያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ዘጠነኛው ለማታንያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ዐሥረኛው ለሺምዒ ወጣ፤ እርሱም፥ ልጆቹም፥ ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ዐሥራ አንደኛው ለዓዛርኤል ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ዐሥራ ሁለተኛው ለሐሻብያ ወጣ፥ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ዐሥራ ሦስተኛው ለሹባኤል ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ዐሥራ አራተኛ ለማቲትያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ዐሥራ አምስተኛው ለያሪሞት ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ዐሥራ ስድስተኛው ለሐናንያ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ዐሥራ ሰባተኛው ለዮሽበቃሽ ወጣ፥ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ዐሥራ ስምንተኛው ለሐናኒ ወጣ፥ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ዐሥራ ዘጠነኛ ለማሎቲ ወጣ፥ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ኻያኛ ለኤሊአታ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ኻያ አንደኛ ለሆቲር ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ኻያ ሁለተኛ ለጊደልቲ ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ኻያ ሦስተኛ ለማሕዚኦት ወጣ፤ እርሱም፥ ወንድሞቹም፥ ልጆቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ። ኻያ አራተኛ ለሮሚምቲዔዜር ወጣ፤ እርሱም ልጆቹም፥ ወንድሞቹም ዐሥራ ሁለት ነበሩ።