1 ዜና መዋዕል 24:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ዕጣውንም በቅድሚያ ለማውጣት የአልዓዛርና የኢታማር ዘሮች ተራ ይገቡ ነበር፤ ከዚህም በኋላ በሌዋዊው ጸሐፊ በናትናኤል ልጅ በሸማዕያ ይመዘግቡ ነበር፤ ንጉሡና ባለሟሎቹ የሆኑት ባለሥልጣኖች፥ ካህናቱ ሳዶቅና የአብያታር ልጅ አቤሜሌክ፥ እንዲሁም የካህናትና የሌዋውያን ቤተሰቦች አለቆች ሁሉ ምስክሮች ነበሩ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም6 የሌዋዊው የናትናኤል ልጅ ጸሓፊው ሸማያ በንጉሡና በሹማምቱ፣ በካህኑ በሳዶቅ፣ በአብያታር ልጅ በአቢሜሌክ እንዲሁም በካህናቱና በሌዋውያኑ ቤተ ሰብ አለቆች ፊት ስማቸውን ጻፈ፤ የጻፈውም አንዱን ቤተ ሰብ ከአልዓዛር ሌላውን ደግሞ ከኢታምር በመውሰድ ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ከሌዊያውያንም ወገን የነበረው የናትናኤል ልጅ ጸሐፊው ሸማያ በንጉሡና በሹማምንቱ ፊት፥ በካህኑ በሳዶቅና በአብያታርም ልጅ በአቤሜሌክ ፊት፥ በካህናቱና በሌዋውያኑ አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት ጻፋቸው፤ አንዱንም የአባት ቤት ለአልዓዛር፥ አንዱንም ለኢታምር ተመረጠ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ከሌዋውያንም ወገን የነበረው የናትናኤል ልጅ ጸሓፊው ሳምያስ በንጉሡና በአለቆቹ ፊት ፥ በካህኑ በሳዶቅና በአብያታርም ልጅ በአቤሜሌክ ፊት ፥ በካህናቱና በሌዋውያኑ አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት ጻፋቸው፤ አንዱንም የአባት ቤት ለአልዓዛር፥ አንዱንም ለኢታምር ጻፈ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ከሌዊያውያንም ወገን የነበረው የናትናኤል ልጅ ጸሐፊው ሸማያ በንጉሡና በአለቆቹ ፊት፥ በካህኑ በሳዶቅና በአብያታርም ልጅ በአቤሜሌክ ፊት፥ በካህናቱና በሌዋውያኑ አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት ጻፋቸው፤ አንዱንም የአባት ቤት ለአልዓዛር፥ አንዱንም ለኢታምር ጻፈ። 参见章节 |
ኻያ አራቱ የቤተሰብ ቡድኖች በዕጣ የወጣላቸው የሥራ ምድቡ ክፍፍል ቅደም ተከተል ተራ እንደሚከተለው ነው፦ አንደኛ በይሆያሪብ የሚመራው ቡድን፥ ሁለተኛ በይዳዕያ የሚመራው ቡድን፥ ሦስተኛ በሐሪም የሚመራው ቡድን፥ አራተኛ በሰዖሪም የሚመራው ቡድን፥ አምስተኛ በማልኪያ የሚመራው ቡድን፥ ስድስተኛ በሚያሚን የሚመራው ቡድን፥ ሰባተኛ በሀቆጽ የሚመራው ቡድን፥ ስምንተኛ በአቢያ የሚመራው ቡድን፥ ዘጠነኛ በኢያሱ የሚመራው ቡድን፥ ዐሥረኛ በሸካንያ የሚመራው ቡድን፥ ዐሥራ አንደኛ በኤልያሺብ የሚመራው ቡድን፥ ዐሥራ ሁለተኛ በያቂም የሚመራው ቡድን፥ ዐሥራ ሦስተኛ በሑፓ የሚመራው ቡድን፥ ዐሥራ አራተኛ በዬሼብአብ የሚመራው ቡድን፥ ዐሥራ አምስተኛ በቢልጋ የሚመራው ቡድን፥ ዐሥራ ስድስተኛ በኢሜር የሚመራው ቡድን፥ ዐሥራ ሰባተኛ በሔዚር የሚመራው ቡድን፥ ዐሥራ ስምንተኛ በሃፒጼጽ የሚመራው ቡድን፥ ዐሥራ ዘጠነኛ በፐታሕያ የሚመራው ቡድን፥ ኻያኛ በይሔዝቄል የሚመራው ቡድን፥ ኻያ አንደኛ በያኪን የሚመራው ቡድን፥ ኻያ ሁለተኛ በጋሙል የሚመራው ቡድን፥ ኻያ ሦስተኛ በደላያ የሚመራው ቡድን፥ ኻያ አራተኛ በማዓዝያ የሚመራው ቡድን።