Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 24:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 የአልዓዛር ቤተሰብ ቊጥር ከኢታማር ቤተሰብ ቊጥር በልጦ ስለ ተገኘ አመዳደቡም በዚሁ መሠረት ተወሰነ፤ ስለዚህ የአልዓዛር የቤተሰብ አለቆች ቊጥር ዐሥራ ስድስት ሆኖ ሲደለደል የኢታማር አለቆች ቊጥር ስምንት እንዲሆን ወሰነ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከኢታምር ይልቅ በአልዓዛር ዘሮች መካከል ብዙ መሪዎች ተገኙ፤ አከፋፈላቸውም እንደሚከተለው ነበር፤ ከአልዓዛር ዘሮች ዐሥራ ስድስት የቤተ ሰብ አለቆች፤ ከኢታምርም ዘሮች ስምንት የቤተ ሰብ አለቆች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የአልዓዛርም ልጆች አለቆች ከኢታምር ልጆች አለቆች በልጠው ተገኙ፤ እንዲህም ተመደቡ፤ ከአልዓዛር ልጆች እንደ አባቶቻቸው ቤቶች ዐሥራ ስድስት፥ ከኢታምርም ልጆች እንደ አባቶቻቸው ቤቶች ስምንት አለቆች ነበሩ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 የአ​ል​ዓ​ዛ​ርም ልጆች አለ​ቆች ከኢ​ታ​ምር ልጆች አለ​ቆች በል​ጠው ተገኙ፤ እን​ዲ​ህም ተመ​ደቡ፤ ከአ​ል​ዓ​ዛር ልጆች እንደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች ዐሥራ ስድ​ስት አለ​ቆች፥ ከኢ​ታ​ም​ርም ልጆች እንደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች ስም​ንት አለ​ቆች ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 የአልዓዛርም ልጆች አለቆች ከኢታምር ልጆች አለቆች በልጠው ተገኙ፤ እንዲህም ተመደቡ፤ ከአልዓዛር ልጆች እንደ አባቶቻቸው ቤቶች አሥራ ስድስት፥ ከኢታምርም ልጆች እንደ አባቶቻቸው ቤቶች ስምንት አለቆች ነበሩ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 24:4
7 交叉引用  

እንግዲህ እነዚህ ሁሉ በየጐሣቸውና በየቤተሰባቸው የተዘረዘሩት የሌዊ ዘሮች ሲሆኑ፥ እያንዳንዳቸው በየስማቸው ተጠቅሰዋል። ኻያ ዓመት የሞላው ወይም ከዚያ በላይ የሆነው እያንዳንዱ የሌዊ ዘር በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ባለው ሥራ ድርሻ ነበረው።


ንጉሥ ዳዊት የአሮንን ዘሮች እንደየሥራ ምድባቸው በቡድን በቡድን ከፈላቸው፤ ይህንንም ያደረገው የአልዓዛር ዘር በሆነው በሳዶቅና የኢታማር ዘር በሆነው በአቤሜሌክ ረዳትነት ነው።


በአልዓዛርና በኢታማር ዘሮች መካከል የቤተ መቅደስ ባለሥልጣኖችና መንፈሳውያን መሪዎች ይገኙ ስለ ነበር፥ የሥራ መደብ ክፍፍል የሚደረገው በዕጣ ነበር።


ንጉሥ ሰሎሞን ለእስራኤላውያን ሁሉ፥ ለሺህ አለቆችና ለመቶ አለቆች፥ እንዲሁም ለመንግሥቱ ባለ ሥልጣኖች፥ ለቤተሰብ መሪዎችና ሕዝብ በሙሉ፥


ዮያቂም ሊቀ ካህናት በነበረበት ዘመን ከዚህ የሚከተሉት ካህናት፥ የካህናት ጐሣዎች አለቆች ነበሩ፦ ካህኑ ጐሣው። መራያ ሠራያ። ሐናንያ ኤርምያስ። መሹላም ዕዝራ። የሆሐናን አማርያ። ዮናታን መሉኪ። ዮሴፍ ሸካንያ። ዓድና ሓሪም። ሔልቃይ መራዮት። ዘካርያስ ዒዶ። መሹላም ጊነቶን። ዚክሪ አቢያ። ሚንያሚን ፒልጣይ ሞዓዲያ። ሻሙዐ ቢልጋ። የሆናታን ሸማዕያ። ማትናይ ዮያሪብ። ዑዚ ይዳዕያ። ቃላይ ሳላይ። ዔቤር ዓሞቅ። ሐሻብያ ሒልቂያ። ናትናኤል ይዳዕያ።


跟着我们:

广告


广告