Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 23:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30-31 ዘወትር ጠዋትና ማታ፥ እንዲሁም ለእግዚአብሔር መባ ሆኖ የሚቀርበው ነገር በሚቃጠልበት በየሰንበቱ፥ በየወሩ መባቻና በሌሎችም በዓላት እግዚአብሔርን ማመስገንና ማክበር የእነርሱ ተግባር ነበር፤ በየጊዜው ይህን አገልግሎት የሚፈጽሙ ሌዋውያን ቊጥራቸው ምን ያኽል መሆን እንደሚገባው ደንቦች ነበሩ፤ ሌዋውያን እግዚአብሔርን ለማምለክ በሚደረገው ሥነ ሥርዓት ለሁልጊዜ ተመድበዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 በየዕለቱም እግዚአብሔርን ለማመስገንና ለመወደስ ጧት ጧት ይቆሙ ነበር፤ ይህንም ማታ ማታ

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 እንዲሁም በየጥዋቱና በየማታው ቆመው ጌታን በማመስገንና በማክበር፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 በየ​ጥ​ዋ​ቱና በየ​ማ​ታው ቆመው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለማ​መ​ስ​ገ​ንና ለማ​ክ​በር፥

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ሥራቸውም በየጥዋቱና በየማታው ቆመው እግዚአብሔርን ለማመስገንና ለማክበር፥

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 23:30
19 交叉引用  

ለእግዚአብሔር መባ ሆኖ ለሚቀርበው ኅብስትና ዱቄት፥ ያለ እርሾ ለሚጋገረው ቂጣና በወይራ ዘይት ለሚለወሰው ዱቄት ኀላፊዎች ሲሆኑ፥ ለቤተ መቅደስ መባ ሆኖ የሚቀርበውን ሁሉ የሚመዝኑና የሚለኩ እነርሱ ነበሩ፤


አራት ሺህ የሚሆኑ ደግሞ ለዘብ ጥበቃ ተመደቡ፤ ሌሎች አራት ሺህ ደግሞ ንጉሡ በሚሰጣቸው የሙዚቃ መሣሪያ እግዚአብሔርን በዝማሬ ለማመስገን ተመደቡ።


ቤተ መቅደሱን የመጠበቅና በየማለዳው የቅጽር በሮችን የመክፈት ተግባር የእነርሱ በመሆኑ እነርሱ የሚያድሩት በቤተ መቅደሱ አካባቢ ነበር።


ሌሎች የሌዋውያን ቤተሰቦች አለቆች መዘምራን ነበሩ፤ እነርሱ ሌት ተቀን የማገልገል ኀላፊነት ስለ ነበረባቸው ከሌሎች አገልግሎቶች ነጻ በመሆን በቤተ መቅደሱ ቅጽር ግቢ በተዘጋጁላቸው ክፍሎች ውስጥ ይኖሩ ነበር።


ንጉሥ ሕዝቅያስ የካህናትንና የሌዋውያንን ሥርዓት እንደገና አቋቋመ፤ በዚህም ጉባኤ ውስጥ እያንዳንዱ ካህንና እያንዳንዱ ሌዋዊ የተለየ የሥራ ምድብ ነበረው፤ ይህም የሥራ ምድብ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕትን ማቅረብን፥ በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሚከናወነው የአምልኮ ሥነ ሥርዓት መሳተፍን፥ በሌሎቹም በቤተ መቅደሱ ልዩ ልዩ ክፍሎች ምስጋናና ውዳሴ ማቅረብን የሚያጠቃልል ነበር፤


በዙፋኑና በአራቱ እንስሶች፥ በሽማግሌዎችም ፊት መቶ አርባ አራቱ ሺህ ሰዎች አዲስ መዝሙር ዘመሩ፤ ይህን መዝሙር ከምድር ከተዋጁት ከመቶ አርባ አራቱ ሺህ ሰዎች በቀር ማንም ሊማረው አልቻለም።


跟着我们:

广告


广告