Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 23:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ እግዚአብሔር የሚመለክበትን ድንኳንና ለአምልኮ ሥነ ሥርዓት መገልገያ የሆኑትን ዕቃዎች ሌዋውያን መሸከም አይኖርባቸውም።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ሌዋውያን ከእንግዲህ ወዲህ ድንኳኑን ወይም የመገልገያ ዕቃውን ሁሉ መሸከም የለባቸውም።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ሌዋውያንም ከእንግዲህ ወዲህ ማደሪያውንና የመገልገያውን ዕቃ ሁሉ አይሸከሙም።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ሌዋ​ው​ያ​ንም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ማደ​ሪ​ያ​ው​ንና የማ​ገ​ል​ገያ ዕቃ​ውን ሁሉ አይ​ሽ​ከ​ሙም።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ሌዋውያንም ከእንግዲህ ወዲህ ማደሪያውንና የማገልገያውን ዕቃ ሁሉ አይሸከሙም፤” አለ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 23:26
7 交叉引用  

ዳዊት ለመጨረሻ ጊዜ በሰጠው መመሪያ መሠረት ሌዋውያን ሁሉ ኻያ ዓመት የሞላቸውና ከዚያ በላይ የሆኑ ተመዘገቡ፤


እንዲሁም ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ለለዩ፥ የመላው እስራኤል መምህራን ለሆኑ ሌዋውያን እንዲህ የሚል መመሪያ ሰጠ፦ “የተቀደሰውን የቃል ኪዳን ታቦት የዳዊት ልጅ የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን ባሠራው ቤተ መቅደስ ውስጥ አኑሩት፤ ከእንግዲህ ወዲህ እናንተ አምላካችሁን እግዚአብሔርንና ሕዝቡን እስራኤልን ማገልገል እንጂ፥ የቃል ኪዳኑን ታቦት በትከሻችሁ ተሸክማችሁ ከስፍራ ወደ ስፍራ መውሰድ የለባችሁም።


ከሰፈር በሚነሡበትም ጊዜ አሮንና ልጆቹ ንዋያተ ቅድሳቱንና የእነርሱንም መገልገያ ዕቃዎች ሁሉ ከሸፈኑ በኋላ የቀዓት ልጆች መጥተው ይሸከሙአቸው፤ ነገር ግን እንዳይሞቱ ንዋያተ ቅድሳቱን መንካት አይገባቸውም፤ እንግዲህ የመገናኛው ድንኳን በሚነሣበት ጊዜ ሁሉ የቀዓት ልጆች ኀላፊነት ይህ ነው።


በዚህም ዐይነት እያንዳንዱ ሰው እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ተቈጠረ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር ለሙሴ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት እያንዳንዱ የማገልገልንና የመሸከምን ኀላፊነት ተቀበለ።


“ሕዝቡ ከሰፈረበት ቦታ በሚነሣበት ጊዜ አሮንና ልጆቹ ወደ ድንኳኑ ገብተው፥ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ለፊት ያለውን መጋረጃ በማውረድ የኪዳኑን ታቦት በእርሱ ይጠቅልሉት።


በእነርሱ ኀላፊነት የሚጠበቁት ንዋያተ ቅድሳት በትከሻቸው የሚሸከሙአቸው ስለ ሆኑ ሙሴ ለቀዓታውያን ሠረገሎችንም ሆነ በሬዎችን አልሰጣቸውም።


በዚያን ጊዜ፥ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት እንዲሸከሙ፥ በፊቱም በመቆም እንዲያገለግሉትና ሕዝቡን በእግዚአብሔር ስም እንዲባርኩ የሌዊን ነገድ በመለየት ሾመ፤ እስከ ዛሬም ድረስ የሌዊ ነገድ ትውልድ አገልግሎት ይኸው ነው።


跟着我们:

广告


广告