Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 21:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ኦርናም “ንጉሥ ሆይ፥ ውሰደው፤ የፈለግኸውንም አድርግበት፤ በመሠዊያው ላይ መሥዋዕት ሆነው እንዲቃጠሉ እነዚህን በሬዎች ጨምረህ ውሰድ፤ እነዚህም የእህል መውቂያ እንጨቶች ለማገዶ ይሁኑልህ፤ ስንዴውንም መባ አድርገህ አቅርበው፤ እነሆ ሁሉንም ለአንተ ሰጥቼሃለሁ” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ኦርናም ዳዊትን፣ “እንዲሁ ውሰደው፤ ጌታዬ ንጉሥ ደስ ያለውን ያድርግ። እነሆ፤ ለሚቃጠል መሥዋዕት በሬዎቹን፣ ለሚነድደውም ዕንጨት መውቂያ በትሮቹን፣ ስንዴውን ደግሞ ለእህል ቍርባን እንዲሆን እሰጣለሁ፤ ሁሉንም እኔ እሰጣለሁ” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ኦርናም ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “ለአንተ ውሰደው፥ ጌታዬ ንጉሡም ደስ የሚያሰኘውን ያድርግ፤ እነሆ፥ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሬዎቹን፥ ለማገዶም የአውድማውን መውቅያ፥ ለእህልም ቁርባን ስንዴውን እሰጥሃለሁ፤ ሁሉን እሰጣለሁ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ኦር​ናም ዳዊ​ትን፥ “ለአ​ንተ ውሰ​ደው፤ ጌታዬ ንጉ​ሡም በፊቱ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን ያድ​ርግ፤ እነሆ፥ ለሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት በሬ​ዎ​ቹን፥ ለእ​ን​ጨ​ትም የአ​ው​ድ​ማ​ውን ዕቃ፥ ለእ​ህ​ልም ቍር​ባን ስን​ዴ​ውን እሰ​ጥ​ሀ​ለሁ፥ ሁሉን እሰ​ጣ​ለሁ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ኦርናም ዳዊትን “ለአንተ ውሰደው፤ ጌታዬ ንጉሡም ደስ የሚያሰኘውን ያድርግ፤ እነሆ፥ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሬዎቹን፥ ለእንጨትም የአውድማውን ዕቃ፥ ለእህልም ቍርባን ስንዴውን እሰጥሃለሁ፤ ሁሉን እሰጣለሁ፤” አለው።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 21:23
8 交叉引用  

ከዚህ በኋላ ኤልሳዕ ወደ ጥማድ በሬዎቹ ተመልሶ ዐረዳቸው፤ የተጠመዱበትንም ቀንበር በማንደድ ሥጋቸውን ቀቅሎ ለሰዎቹ አቀረበላቸው፤ እነርሱም በሉ፤ ከዚህ በኋላ ኤልያስን ተከትሎ በመሄድ ረዳቱ ሆነ።


ዳዊትም “ቸነፈሩ ይወገድ ዘንድ ለእግዚአብሔር መሠዊያ እንድሠራበት አውድማህን ሽጥልኝ፤ እኔም ሙሉ ዋጋ እሰጥሃለሁ” አለው።


ንጉሥ ዳዊት ግን “ይህስ አይሆንም፤ ሙሉውን ዋጋ እከፍልሃለሁ፤ የአንተ ንብረት የሆነውን፥ እኔ ምንም ዋጋ ያልከፈልኩበትን ነገር ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጌ ማቅረብ አልፈልግም” ሲል መለሰለት።


እግዚአብሔር በተናገረው መሠረት ሐናምኤል ታስሬ ወዳለሁበት ወደ ዘብ ጠባቂዎች ክፍል መጥቶ “የመግዛት መብት ያንተ ስለ ሆነ መሬቴን ግዛ” አለኝ፤ ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር እንደ ተናገረኝ ዐወቅሁ።


ሠረገላውም በቤትሼሜሽ ወደሚኖር ኢያሱ ተብሎ ወደሚጠራው ሰው እርሻ መጥቶ በትልቅ ቋጥኝ አጠገብ ሲደርስ ቆመ። ሕዝቡም የሠረገላውን እንጨት ፈለጡ፤ ላሞቹንም ዐርደው ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው አቀረቡአቸው።


跟着我们:

广告


广告