Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 21:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ዳዊትም “ቸነፈሩ ይወገድ ዘንድ ለእግዚአብሔር መሠዊያ እንድሠራበት አውድማህን ሽጥልኝ፤ እኔም ሙሉ ዋጋ እሰጥሃለሁ” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ዳዊትም ኦርናን፣ “በሕዝቡ ላይ የወረደው መቅሠፍት እንዲወገድ ለእግዚአብሔር መሠዊያ እሠራ ዘንድ ዐውድማህን ልውሰደው፤ ሙሉውን ዋጋ እከፍልሃለሁ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ዳዊትም ኦርናን፦ “በላዩ ለጌታ መሠዊያ እንድሠራ ይህን የአውድማ ስፍራ ስጠኝ፤ ሙሉ ዋጋ ልክፈልና ስጠኝ፤ መቅሰፍቱም ከሕዝቡ ይከለከላል” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ዳዊ​ትም ኦር​ናን፥ “በላዩ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ እሠራ ዘንድ ይህን የአ​ው​ድማ ስፍራ ስጠኝ፤ በሙሉ ዋጋ ሽጥ​ልኝ፤ መቅ​ሠ​ፍ​ቱም ከሕ​ዝቤ ይከ​ለ​ከ​ላል” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ዳዊትም ኦርናን “በላዩ ለእግዚአብሔር መሠዊያ እሠራ ዘንድ ይህን የአውድማ ስፍራ ስጠኝ፤ በሙሉ ዋጋ ስጠኝ፤ መቅሰፍቱም ከሕዝቡ ይከለከላል” አለው።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 21:22
8 交叉引用  

በእርሻው ድንበር ላይ ያለችውን ማክፌላ የተባለችውን ድርብ ክፍል ያላትን ዋሻ እንዲሸጥልኝ ጠይቁልኝ፤ ይህ ስፍራ የመቃብር ቦታ እንዲሆንልኝ በእናንተ ፊት ሙሉ ዋጋ ከፍዬ እንድገዛው አድርጉልኝ።”


ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ “አጣድ” ተብላ ወደምትጠራው አውድማ ደረሱ፤ እዚያም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በመጮኽ አለቀሱ፤ ዮሴፍም እዚያ ሰባት ቀን ሙሉ የሐዘን ውሎ አደረገ።


“ንጉሥ ሆይ! ስለምን ወደዚህ መጣህ?” ሲል ጠየቀው። ዳዊትም “እግዚአብሔር የቸነፈሩን መቅሠፍት እንዲመልስ የአንተን አውድማ ለመግዛትና በዚያውም ላይ መሠዊያ ለመሥራት ነው የመጣሁት” አለው።


አንድ ቀን አክዓብ ናቡቴን “የወይን ተክል ቦታህን ስጠኝ፤ በቤተ መንግሥቴ አጠገብ ስለ ሆነ የአትክልት ቦታ ላደርገው እፈልጋለሁ፤ በምትኩ ከእርሱ የተሻለ የወይን ተክል ቦታ እሰጥሃለሁ፤ ልትሸጠው ብትፈልግም የተሻለ ጥሩ ዋጋ እከፍልሃለሁ” አለው።


ኦርናም ዳዊት ወደ እነርሱ እየቀረበ መምጣቱን ባየ ጊዜ ከአውድማው ወጥቶ ወደ መሬት ለጥ በማለት እጅ ነሣ፤


ኦርናም “ንጉሥ ሆይ፥ ውሰደው፤ የፈለግኸውንም አድርግበት፤ በመሠዊያው ላይ መሥዋዕት ሆነው እንዲቃጠሉ እነዚህን በሬዎች ጨምረህ ውሰድ፤ እነዚህም የእህል መውቂያ እንጨቶች ለማገዶ ይሁኑልህ፤ ስንዴውንም መባ አድርገህ አቅርበው፤ እነሆ ሁሉንም ለአንተ ሰጥቼሃለሁ” አለው።


በዚህም መቅሠፍቱ እንዲቆም አደረገ፤ አሮንም በሞቱትና በሕይወት ባሉት መካከል ቆሞ ነበር።


ሰውየውና ሴቲቱ ወዳሉበት ድንኳን ገባ፤ ሁለቱንም በአንድነት በጦር ወግቶ ገደላቸው፤ በዚህም ዐይነት እስራኤላውያንን በማጥፋት ላይ የነበረው መቅሠፍት ቆመ፤


跟着我们:

广告


广告