1 ዜና መዋዕል 20:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ሌላም ጦርነት በጋት ተደረገ፤ በዚያም ጦርነት በእያንዳንዱ እጅና በእያንዳንዱ እግር ላይ ስድስት ስድስት በጠቅላላ ኻያ አራት ጣቶች የነበሩት አንድ ረጅም ሰው ነበር፤ እርሱም ኀያላን ከሆኑት ከራፋይም ዘር ነበር፤ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ደግሞም ጋት ላይ በተደረገ ሌላ ጦርነት፣ በእጆቹና በእግሮቹ ላይ ስድስት ስድስት ጣት በድምሩ ሃያ አራት ጣት የነበሩት አንድ ግዙፍ ሰው ነበረ፤ ይህም እንደዚሁ ከራፋይም ዘር ነበረ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ደግሞ በጌት ላይ ጦርነት ተደርጎ ነበረ፤ ከዚያም በእጁና በእግሩ ስድስት ስድስት ባጠቃላይ ሀያ አራት ጣቶች ያሉት አንድ ረጅም ሰው ነበረ፤ እርሱም ደግሞ ከራፋይም የተወለደ ነበረ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ደግሞ በጌት ላይ ሰልፍ ሆነ ፤ በዚያም በእጁና በእግሩ ስድስት ስድስት ጣቶች በጠቅላላው ሃያ አራት ጣቶች ያሉት አንድ ረዥም ሰው ነበረ፤ እርሱም ደግሞ ከኀያላን የተወለደ ነበረ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ደግሞ በጌት ላይ ሰልፍ ነበረ፤ ከዚያም በእጁና በእግሩ ስድስት ስድስት ባጠቃላይ ሃያ አራት ጣቶች ያሉት አንድ ረጅም ሰው ነበረ፤ እርሱም ደግሞ ከራፋይም የተወለደ ነበረ። 参见章节 |