Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 20:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በተከታዩ የዓመት መባቻ ማለትም ነገሥታት አብዛኛውን ጊዜ ወደ ጦርነት በሚሄዱበት ወራት፥ ኢዮአብ ሠራዊቱን እየመራ ሄዶ የዐሞንን አገር ወረረ፤ ንጉሥ ዳዊት ግን በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር፤ የኢዮአብ ሠራዊትም የራባን ከተማ ከበው አደጋ በመጣል ደመሰሱአት፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ነገሥታት ለጦርነት በሚወጡበት በጸደይ ወራት፣ ኢዮአብ የጦር ሰራዊቱን እየመራ ሄዶ የአሞናውያንን አገር አጠፋ፤ ወደ ረባትም ሄዶ ከበባት፤ ዳዊት ግን በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር። ኢዮአብም ረባትን ወግቶ አፈራረሳት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 እንዲህም ሆነ፤ በዓመት መለወጫ ነገሥታት ወደ ጦርነት በሚወጡበት ጊዜ ኢዮአብ ሠራዊቱን አወጣ፥ የአሞንንም ልጆች አገር አጠፋ፤ መጥቶም ረባትን ከበበ። ዳዊትም በኢየሩሳሌም ቈይቶ ነበር። ኢዮአብም ረባትን መትቶ አፈረሳት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዓ​መት መጨ​ረሻ ነገ​ሥ​ታት ወደ ሰልፍ በሚ​ወ​ጡ​በት ጊዜ ኢዮ​አብ የሠ​ራ​ዊ​ቱን ኀይል አወጣ፤ የአ​ሞ​ን​ንም ልጆች ሀገር አጠፋ፤ መጥ​ቶም አራ​ቦ​ትን ከበበ። ዳዊ​ትም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተቀ​ምጦ ነበር። ኢዮ​አ​ብም አራ​ቦ​ትን መትቶ አፈ​ረ​ሳት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እንዲህም ሆነ፤ በዓመት መለወጫ ነገሥታት ወደ ሰልፍ በሚወጡበት ጊዜ ኢዮአብ ሠራዊቱን አወጣ፤ የአሞንንም ልጆች አገር አጠፋ፤ መጥቶም ረባትን ከበበ። ዳዊትም በኢየሩሳሌም ቈይቶ ነበር። ኢዮአብም ረባትን መትቶ አፈረሳት።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 20:1
15 交叉引用  

የዓመት መጀመሪያ በሆነው በጸደይ ወራት፥ በተለምዶ ነገሥታት ወደ ጦርነት በሚዘምቱበት ጊዜ፥ ዳዊት ኢዮአብን ከጦር መኰንኖቹና ከመላው የእስራኤል ሠራዊት ጋር አዘመተው፤ እነርሱም ዐሞናውያንን ድል ነሥተው ራባ ተብላ የምትጠራውን ከተማ ከበቡ፤ ዳዊት ግን በኢየሩሳሌም ቈየ።


ዳዊት ማሕናይም በደረሰ ጊዜ በዐሞን ግዛት ራባ ተብላ ከምትጠራው ከተማ የመጣውን የናዖስን ልጅ ሾቢን፥ ከሎደባር ከተማ የመጣውን የዓሚኤልን ልጅ ማኪርንና ከገለዓድ ግዛት ሮገሊም ተብላ ከምትጠራው ከተማ የመጣውን ባርዚላይን አገኘ።


ከዚህ በኋላ ነቢዩ ወደ ንጉሥ አክዓብ ቀርቦ የሶርያ ንጉሥ በሚመጣው የጸደይ ወራት እንደገና አደጋ ስለሚጥልብህ “ተመልሰህ ሂድና ሠራዊትህን በማጠናከር አደራጅ፤ ጥንቃቄ የሞላበትንም የጦርነት ስልት አዘጋጅ” አለው።


ስለዚህም በተከታዩ የጸደይ ወቅት ሠራዊቱን በአንድነት ጠርቶ በእስራኤል ላይ አደጋ ለመጣል ወደ አፌቅ ከተማ ገሠገሠ፤


ኤልሳዕም ሞተ፤ ተቀበረም። ከሞአብ የሚመጡ አደጋ ጣዮች በየዓመቱ የእስራኤልን ምድር ይወሩ ነበር።


በሀዳድዔዜር ሥልጣን ሥር የነበሩት ነገሥታት በእስራኤል ድል እንደ ተመቱ በተገነዘቡ ጊዜ ከዳዊት ጋር የሰላም ስምምነት አድርገው የእርሱ ገባሮች ሆኑ፤ ከዚያን በኋላም ሶርያውያን ዐሞናውያንን ለመርዳት ፈቃደኞች አልሆኑም።


“እነሆ፥ በወናፉ ፍሙን የሚያናፋውን ብረት አቅላጭ የፈጠርኩ እኔ ነኝ፤ እርሱም መሣሪያውን የሚሠራው ለየተሠራለት ዓላማ እንዲውል ለማድረግ ነው፤ ያጠፋ ዘንድ አጥፊውን የፈጠርኩ እኔ ነኝ።


እኔም “አቤቱ ጌታ ሆይ፥ ይህ የሚሆነው እስከ መቼ ነው?” ብዬ ጠየቅሁ። እርሱም “ከተሞች እስኪፈርሱ፥ ቤቶችም የሚኖርባቸው አጥተው ወና እስኪሆኑና አገሪቱም የተፈታች ባድማ እስክትሆን ድረስ ነው።


ለጦሩ ወደ አሞናውያን ከተማ ራባ በሚወስደው መንገድ ላይና እንዲሁም ወደ ተመሸገችው የይሁዳ ከተማ ወደ ኢየሩሳሌም በሚወስደው መንገድ ላይ የአቅጣጫ ምልክት አድርግ።


የራባን ከተማ የግመሎች ማሰማርያ፥ መላውንም የዐሞን አገር የበጎች መዋያ አደርገዋለሁ፤ በዚህም ዐይነት እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።


ስለዚህ በራባ ከተማ ቅጽር ላይ እሳት እለቅበታለሁ፤ ምሽጎችዋንም ያቃጥላል፤ ከዚህ በኋላ በጦርነቱ ቀን ጩኸትና ሁካታ ይበዛል፤ ጦርነቱም እንደ ዐውሎ ነፋስ ይፈጥናል፤


ከረፋያውያን ወገን ንጉሥ ዖግ የመጨረሻው ነበር፤ አልጋው ከብረት የተሠራ ሆኖ በይፋ በታወቀው መለኪያ ቁመቱ አራት ሜትር፥ የጐኑም ስፋት ሁለት ሜትር ያኽል ነበር። እርሱም ራባ ተብላ በምትጠራው በዐሞናውያን ከተማ እስከ አሁን ይታያል።


跟着我们:

广告


广告