Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 19:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 በሀዳድዔዜር ሥልጣን ሥር የነበሩት ነገሥታት በእስራኤል ድል እንደ ተመቱ በተገነዘቡ ጊዜ ከዳዊት ጋር የሰላም ስምምነት አድርገው የእርሱ ገባሮች ሆኑ፤ ከዚያን በኋላም ሶርያውያን ዐሞናውያንን ለመርዳት ፈቃደኞች አልሆኑም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 የአድርአዛርም ሹማምት በእስራኤል መሸነፋቸውን ሲያዩ፣ ከዳዊት ጋራ ታረቁ፤ ገባሮቹም ሆኑ። ስለዚህ ሶርያውያን ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አሞናውያንን ለመርዳት ፈቃደኞች አልሆኑም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 የአድርአዛርም ባርያዎች በእስራኤል ፊት እንደ ተሸነፉ ባዩ ጊዜ ከዳዊት ጋር ታረቁ፥ ገበሩለትም፤ ሶርያውያንም ከዚያ ወዲያ የአሞንን ልጆች ለመርዳት እንቢ አሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 የአ​ድ​ር​አ​ዛ​ርም አገ​ል​ጋ​ዮች በእ​ስ​ራ​ኤል ፊት እንደ ተሸ​ነፉ ባዩ ጊዜ ከዳ​ዊት ጋር ታረቁ፤ ተገ​ዙ​ለ​ትም፤ ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ከዚያ ወዲያ የአ​ሞ​ንን ልጆች ይረዱ ዘንድ እንቢ አሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 የአድርአዛርም ባሪያዎች በእስራኤል ፊት እንደ ተሸነፉ ባዩ ጊዜ ከዳዊት ጋር ታረቁ፤ ገበሩለትም፤ ሶርያውያንም ከዚያ ወዲያ የአሞንን ልጆች ይረዱ ዘንድ “እንቢ” አሉ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 19:19
13 交叉引用  

ከጥቂት ጊዜ በኋላ የዐሞን ንጉሥ ስለ ሞተ፥ ልጁ ሐኑን በእርሱ እግር ተተክቶ ነገሠ፤


በሀዳድዔዜር ሥልጣን ሥር የነበሩት ነገሥታት በእስራኤላውያን ድል መመታታቸውን በተገነዘቡ ጊዜ ከእነርሱ ጋር የሰላም ስምምነት አድርገው የእስራኤላውያን ተገዢዎች ሆኑ፤ ከዚያም በኋላ ሶርያውያን ዳግመኛ ዐሞናውያንን ለመርዳት ፈሩ።


የሶርያ ንጉሥ ቤንሀዳድ መላ ሠራዊቱን በአንድነት ሰበሰበ፤ ብዙ ፈረሶችና ሠረገሎች ባሉአቸው ሠላሳ ሁለት ነገሥታት ተደግፎ በመዝመት የእስራኤል ዋና ከተማ የሆነችውን ሰማርያን ከቦ አደጋ ጣለባት።


ቤንሀዳድና የእርሱ የጦር ቃል ኪዳን ጓደኞቹ የሆኑ ሌሎችም ነገሥታት በድንኳኖቻቸው ውስጥ ሆነው ሲጠጡ ሳሉ የአክዓብ መልእክት ደረሰ፤ በዚህን ጊዜ ቤንሀዳድ በከተማይቱ ላይ አደጋ ለመጣል እንዲዘጋጁ ትእዛዝ ሰጠ፤ ስለዚህም እነርሱ ፈጥነው በመንቀሳቀስ ቦታ ቦታቸውን ያዙ።


የዳዊትም ዝና በየቦታው ተሠራጨ፤ እግዚአብሔርም ዳዊት በሕዝቦች ሁሉ ዘንድ የተፈራ እንዲሆን አደረገ።


እስራኤላውያንም ሶርያውያንን ወደ ኋላ መልሰው አባረሩአቸው፤ ዳዊትና ሠራዊቱ ሰባት ሺህ ሠረገላ ነጂዎችን፥ አርባ ሺህ እግረኛ ወታደሮችን ገደሉ፤ እንዲሁም ሾባክ ተብሎ የሚጠራውን የሶርያውያንን የጦር አዛዥ ገደሉ፤


በተከታዩ የዓመት መባቻ ማለትም ነገሥታት አብዛኛውን ጊዜ ወደ ጦርነት በሚሄዱበት ወራት፥ ኢዮአብ ሠራዊቱን እየመራ ሄዶ የዐሞንን አገር ወረረ፤ ንጉሥ ዳዊት ግን በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር፤ የኢዮአብ ሠራዊትም የራባን ከተማ ከበው አደጋ በመጣል ደመሰሱአት፤


ለጦርነት ኀይልን ትሰጠኛለህ፤ በጠላቶቼም ላይ ድልን ታጐናጽፈኛለህ።


ባዕዳን ያጐነብሱልኛል፤ ዝናዬን እንደ ሰሙም ይገዙልኛል።


ስለዚህም ንጉሣቸው እንዲህ እያለ ይደነፋል፥ “የጦር አዛዦቼ ሁሉ ነገሥታት አይደሉምን?


跟着我们:

广告


广告