Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 17:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ስለዚህ በፊትህ ለዘለዓለም ይኖር ዘንድ የእኔን የባሪያህን ቤት እንድትባርክ ፈቃድህ ይሁን፤ ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ቤተሰቤን ባርከኸዋል፤ እርሱም ለዘለዓለም የተባረከ ይሆናል።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 በፊትህ ለዘላለም እንዲኖር አሁንም የባሪያህን ቤት ልትባርክ ወድደሃል፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ የባረክኸው አንተ ስለ ሆንህ፣ ለዘላለም የተባረከ ይሆናል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ስለዚህ አሁን በፊትህ ለዘለዓለም እንዲኖር የባርያህን ቤት ለመባረክ ፈቅደሃል፤ አንተም፥ አቤቱ፥ አንተ የባረከው ለዘለዓለም ይባረካል።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 አሁ​ንም በፊ​ትህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖር ዘንድ የአ​ገ​ል​ጋ​ይ​ህን ቤት ትባ​ርክ ዘንድ ጀም​ረ​ሃል፤ አን​ተም አቤቱ፥ ባር​ከ​ኸ​ዋል፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ቡሩክ ይሆ​ናል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 አሁንም በፊትህ ለዘላለም ይኖር ዘንድ የባሪያህን ቤት እንድትባርክ ፈቅደሃል፤ አንተም፥ አቤቱ! ባርከኸዋል፤ ለዘላለምም ቡሩክ ይሆናል።”

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 17:27
12 交叉引用  

ይስሐቅም እጅግ ደንግጦ እየተንቀጠቀጠ “ታዲያ፥ አውሬ አድኖ ያመጣልኝ ማን ነበር? ልክ አንተ ከመምጣትህ በፊት ተመገብኩ፤ የመጨረሻ ምርቃቴንም ሰጠሁት፤ ምርቃቱም የእርሱ ሆኖ ይኖራል” አለው።


ኢዮአብ እነዚህን ሰዎች በመግደሉ በእርሱ ላይ የተፈጸመበት ቅጣት በእርሱና በዘሮቹ ላይ ለዘለዓለም ጸንቶ ይኑር፤ በዙፋኑ ላይ ለሚቀመጡት ለዳዊት ዘሮች ግን የእግዚአብሔር ሰላም ለዘለዓለም አይለያቸው።”


እኔን ግን እግዚአብሔር ይባርከኛል፤ የዳዊት መንግሥትም ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል።”


እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ እውነተኛ አምላክ ነህ፤ ይህንንም አስደናቂ የተስፋ ቃል ለእኔ ሰጥተኸኛል፤


ጥቂት ዘግየት ብሎም ንጉሥ ዳዊት እንደገና በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ በመጣል ድል አደረጋቸው፤ አስገበራቸውም፤ የጋትን ከተማና በዙሪያዋ ያሉትን መንደሮች ከእነርሱ ቊጥጥር ነጻ አደረገ፤


የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፥ ይሁዳን በእስራኤል ላይ መሪ ነገድ አድርጎ መርጦታል፤ ከይሁዳም የእኔን ቤተሰብ፥ ከእኔም ቤተሰብ እኔን የእስራኤል ንጉሥ እንድሆን መረጠኝ፤ የእኔም ዘሮች ነገሥታት ሆነው እንደሚያስተዳድሩ ቃል ገብቶልኛል።


የዘለዓለም በረከትን ሰጠኸው፤ አንተም ከእርሱ ጋር በመገኘትህ ደስ ታሰኘዋለህ፤


የንጉሡ ስም ለዘለዓለሙ ሲታወስ ይኑር፤ ዝናውም ፀሐይ በሚወጣበት ዘመን ሁሉ ይሰማ፤ ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ የተባረኩ ይሁኑ፤ እርሱንም “የተባረከ ነው!” ይሉታል።


እኔ የተነገረኝ እንድመርቅ ነው፤ እግዚአብሔር ሲመርቅ እኔ የእርሱን ቃል መለወጥ አልችልም።


እግዚአብሔር ከመረጠና ጸጋውን ከሰጠ በኋላ ባደረገው ነገር ሐሳቡን አይለውጥም።


በሰማይ ባለው መንፈሳዊ በረከት ሁሉ በክርስቶስ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን።


እግዚአብሔር በሰጠው የተስፋ ቃል መሠረት ይባርክሃል፤ አንተ ለብዙ ሕዝቦች ገንዘብ ታበድራለህ፤ ነገር ግን ከእነርሱ ከማንኛውም ሰው አትበደርም፤ አንተ በብዙ ሕዝቦች ላይ የበላይነት ይኖርሃል፤ በአንተ ላይ ግን ማንም የበላይ አይሆንም።


跟着我们:

广告


广告