Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 13:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ዑዛ ታቦቱን በመንካቱ እግዚአብሔር ተቈጥቶ ወዲያውኑ በሞት ቀሠፈው፤ ስለዚህም ዑዛ በዚያው በእግዚአብሔር ፊት ሞተ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ታቦቱን በእጁ ስለ ነካ፣ የእግዚአብሔር ቍጣ በዖዛ ላይ ነደደ፤ ስለዚህም በዚያው በእግዚአብሔር ፊት ሞተ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የጌታም ቁጣ በዖዛ ላይ ነደደ፥ እጁንም ወደ ታቦቱ ስለዘረጋ ቀሠፈው፤ በዚያም በእግዚአብሔር ፊት ሞተ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዖዛ ላይ ተቈጣ። እጁ​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ስለ ዘረጋ ቀሠ​ፈው፤ በዚ​ያም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሞተ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 የእግዚአብሔርም ቍጣ በዖዛ ላይ ነደደ፤ እጁንም ወደ ታቦቱ ስለዘረጋ ቀሠፈው፤ በዚያም በእግዚአብሔር ፊት ሞተ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 13:10
10 交叉引用  

ያም ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ “ፔሬጽ ዑዛ” ተብሎ ይጠራል፤ እግዚአብሔር ተቈጥቶ ዑዛን ስለ ገደለው ዳዊት እጅግ ተበሳጨ።


ከዚህ በፊት እናንተ ተገኝታችሁ ታቦቱን ባለመሸከማችሁ በተደነገገው ሥርዓት መሠረት ስላላገለገልነው አምላካችን እግዚአብሔር ቀጥቶናል።”


እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ሌዋውያን ታቦቱን በትከሻቸው ላይ በመሎጊያዎች ተሸክመው ሄዱ።


ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር እሳት ልኮ ዕጣን ያጥኑ የነበሩትን ሁለት መቶ ኀምሳ ሰዎች አቃጠለ።


ከሰፈር በሚነሡበትም ጊዜ አሮንና ልጆቹ ንዋያተ ቅድሳቱንና የእነርሱንም መገልገያ ዕቃዎች ሁሉ ከሸፈኑ በኋላ የቀዓት ልጆች መጥተው ይሸከሙአቸው፤ ነገር ግን እንዳይሞቱ ንዋያተ ቅድሳቱን መንካት አይገባቸውም፤ እንግዲህ የመገናኛው ድንኳን በሚነሣበት ጊዜ ሁሉ የቀዓት ልጆች ኀላፊነት ይህ ነው።


ኢያሱም ካህናቱን ጠርቶ “የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸከሙ፤ ከእናንተም ሰባታችሁ እምቢልታ ይዛችሁ ከታቦቱ ፊት ቅደሙ።”


የታቦቱን ውስጣዊ ክፍል በመመልከታቸው እግዚአብሔር ተቈጥቶ ከቤት ሼሜሽ ሰዎች መካከል ሰባ ሰዎችን ገደለ፤ እግዚአብሔርም ይህን ሁሉ እልቂት በመካከላቸው በማድረጉ የቤት ሼሜስ ሰዎች በማዘን አለቀሱ።


跟着我们:

广告


广告