Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 12:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 የእግዚአብሔር መንፈስ የሠላሳዎቹ መሪ በሆነው በዐማሳይ ላይ ወረደ፤ እርሱም፦ “ዳዊት ሆይ! እኛ የአንተ ነን! የእሴይ ልጅ ዳዊት ሆይ! እኛ ከአንተ ጋር ነን! ለአንተና አንተን ለሚረዱ ሁሉ ሰላም ይሁን! እግዚአብሔር ከአንተ ጋር በመሆን ይረዳሃል፤” በማለት ድምፁን ከፍ አድርጎ ጮኸ፤ ዳዊትም እነርሱን በደስታ ተቀብሎ በሠራዊቱ ውስጥ አለቆች አደረጋቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ከዚያም መንፈስ በሠላሳዎቹ አለቃ በዓማሣይ ላይ ወረደ፤ እርሱም እንዲህ አለ፤ “ዳዊት ሆይ፤ እኛ የአንተ ነን፤ የእሴይ ልጅ ሆይ፤ እኛ ከአንተ ጋራ ነን፤ ሰላም ፍጹም ሰላም ለአንተ ይሁን፤ አንተን ለሚረዱም ሁሉ ሰላም ይሁን፤ አምላክህ ይረዳሃልና።” ስለዚህ ዳዊት ተቀበላቸው፤ የሰራዊቱም አለቃ አደረጋቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 መንፈስም በሠላሳው አለቃ በዓማሣይ ላይ ወረደ፥ እርሱም እንዲህ አለ፦ “ዳዊት ሆይ! እኛ የአንተ ነን፤ የእሴይ ልጅ ሆይ! እኛ ከአንተ ጋር ነን፤ አምላክህ ይረዳሃልና ሰላም ሰላም ለአንተ ይሁን፥ ለሚረዱህም ሰላም ይሁን።” ዳዊትም ተቀበላቸው፥ የጭፍራም አለቆች አደረጋቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 መን​ፈ​ስም በሠ​ላ​ሳው አለቃ በዓ​ማ​ሣይ ላይ መጣ፤ እር​ሱም፥ “ዳዊት ሆይ፥ እኛ ያንተ ነን፤ የእ​ሴይ ልጅ ሆይ፥ እኛ ከአ​ንተ ጋር ነን፤ ውጣ አም​ላ​ክህ ይረ​ዳ​ሃ​ልና ሰላም ሰላም ለአ​ንተ ይሁን፤ ለሚ​ረ​ዱ​ህም ሰላም ይሁን” አለ። ዳዊ​ትም ተቀ​በ​ላ​ቸው፤ የጭ​ፍ​ራም አለ​ቆች አደ​ረ​ጋ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 መንፈስም በሠላሳው አለቃ በዓማሣይ ላይ መጣ፤ እርሱም “ዳዊት ሆይ! እኛ የአንተ ነን፤ የእሴይ ልጅ ሆይ! እኛ ከአንተ ጋር ነን፤ አምላክህ ይረዳሃልና ሰላም ሰላም ለአንተ ይሁን፤ ለሚረዱህም ሰላም ይሁን፤” አለ። ዳዊትም ተቀበላቸው፤ የጭፍራም አለቆች አደረጋቸው።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 12:18
31 交叉引用  

ኢታይ ግን ለንጉሡ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ጌታዬ በሚኖርበት ቦታ ሁሉ፥ በሞትም ሆነ በሕይወት እኔ አገልጋይህ በዚያ እንደምገኝ በእግዚአብሔር ስም እንዲሁም በጌታዬ በንጉሡ ሕይወት እምላለሁ።”


አቤሴሎም በኢዮአብ ምትክ ዐማሣ ተብሎ የሚጠራውን ሰው የጦር አዛዥ አድርጎ ሾመ፤ ዐማሣ የእስራኤላዊው የዬቴር ልጅ ነበር፤ እናቱም አቢጌል ተብላ የምትጠራ የናሐሽ ልጅ ስትሆን ለኢዮአብ እናት ለጸሩያ እኅት ነበረች። ዜና መ. 2፥17


እንዲሁም ለዐማሳ ሲናገር “አንተም ለእኔ የሥጋ ዘመድ ነህ፤ ከአሁን ጀምሮ በኢዮአብ ምትክ የሠራዊቴ አዛዥ አደርግሃለሁ፤ ይህንንም ባላደርግ እግዚአብሔር በሞት ይቅጣኝ!” ብላችሁ ንገሩት ሲል አዘዛቸው።


ከአሁን በፊት ሳኦል የእኛ ንጉሥ በነበረ ጊዜ እንኳ በጦርነት እስራኤልን የምትመራ አንተ ነበርክ፤ እንዲሁም ሕዝቡን እስራኤልን እንድትመራና በእስራኤልም ላይ እንድትነግሥ እግዚአብሔር ቃል ገብቶልሃል።”


ሰሎሞን ከእስራኤላውያን ወገን ማንንም ባሪያ አድርጎ አላሠራም፤ እነርሱ ባለሥልጣኖች፥ ወታደሮች፥ የጦር መኰንኖች፥ የጦር አዛዦች፥ ሠረገላ ለሚነዱ ሁሉ ኀላፊዎችና ፈረሰኞች ሆነው ያገለግሉ ነበር።


ኢዩ ተነሥቶ እንደገና ጒዞ ቀጠለ፤ በመንገድ ሳለም የሬካብን ልጅ ኢዮናዳብን አገኘ፤ ኢዩም ሰላምታ ከሰጠው በኋላ “እኔና አንተ በሐሳብ አንድ ነን፤ ታዲያ ከእኔ ጋር ትተባበራለህን?” ሲል ጠየቀው። ኢዮናዳብም “አዎ እተባበርሃለሁ” ሲል መለሰ። ኢዩም “እንግዲያውስ ጨብጠኝ” ሲል መለሰለት፤ እጅ ለእጅ ተያይዘው ኢዩ ደግፎት በሠረገላው ላይ አስቀመጠውና፥


ስለዚህም የቤተ መንግሥቱ ኀላፊና የከተማይቱ ገዢ ከታወቁ የአገር ሽማግሌዎችና ከአሳዳጊ ሞግዚቶች ጋር በመተባበር ለኢዩ “እኛ አገልጋዮችህ ነን፤ አንተ የምታዘንን ሁሉ ለመፈጸም ዝግጁዎች ነን፤ እኛ ማንንም አናነግሥም፤ አንተ መልካም መስሎ የታየህን አድርግ” ሲሉ መልእክት ላኩ።


ኢዩ ቀና ብሎ ወደ ላይ በመመልከት ድምፁን ከፍ አድርጎ “ከእኔ ጋር የሚተባበር ማን ነው?” ሲል ጮኸ፤ ቊጥራቸው ከሁለት እስከ ሦስት የሆነ የቤተ መንግሥት ባለ ሥልጣኖች በመስኮት ብቅ ብለው ወደ እርሱ ተመለከቱ፤


የመጀመሪያው የሐክሞን ጐሣ ወገን የሆነው ያሾብዓም ሲሆን፥ እርሱም የሦስቱ ኀያላን መሪ ነበር፤ እርሱ በሦስት መቶ ሰዎች ላይ ጦሩን አንሥቶ በአንድ ፍልሚያ ብቻ ሁሉንም ገደላቸው፤


ዳዊትም ወደ እነርሱ ቀርቦ እንዲህ አላቸው፤ “ወደዚህ የመጣችሁት በወዳጅነት ልትረዱኝ ከሆነ መልካም ነው፤ በደስታ እቀበላችኋለሁ፤ ከእኛም ጋር ሁኑ! እኔ ምንም ሳላደርጋችሁ ለጠላቶቼ አሳልፋችሁ ልትሰጡኝ ከሆነ ግን የቀድሞ አባቶቻችን አምላክ ተመልክቶ ይፍረደው።”


ሌላይቱ የእሴይ ሴት ልጅ አቢጌል የእስማኤል ዘር የሆነውን ዬቴርን አግብታ ዐማሣ ተብሎ የሚጠራውን ወንድ ልጅ ወለደች።


እርሱ ጽድቅን እንደ ደረት ጥሩር፥ ማዳንንም እንደ ራስ ቊር ይለብሳል፤ በቀልን እንደ ልብስ ይጐናጸፋል፤ ቊጣንም እንደ ካባ ይደርባል።


በእነዚያ ቀኖች ዐሥር የሌላ አገር ሰዎች ወደ አንድ አይሁዳዊ ቀርበው የልብሱን ዘርፍ በመያዝ ‘እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር መሆኑን ስለ ሰማን ከእናንተ ጋር እንሂድ’ ይሉታል።”


ከእኔ ጋር ያልሆነ ሁሉ ተቃዋሚዬ ነው፤ ከእኔም ጋር የማይሰበስብ ይበትናል።


ይህን መመሪያ ለሚከተሉ ሁሉና የእግዚአብሔር ወገኖች ለሆኑት እስራኤላውያን ሰላምና ምሕረት ይሁን።


በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በዳን ሰፈር ውስጥ በነበረበት ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ ያበረታው ጀመር።


የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ ዐደረ፤ በእስራኤልም ላይ መሪ ሆነ፤ ለጦርነት በወጣ ጊዜ እግዚአብሔር የመስጴጦምያውን ንጉሥ ኩሻን ፊሽዓታይምን አሳልፎ ሰጠው፤ እርሱም ኩሻን ሪሽዓታይምን ድል አደረገው።


የእግዚአብሔር መንፈስ በጌዴዎን ላይ ወረደ፤ የአቢዔዜር ጐሣ ሰዎች ሁሉ እንዲከተሉት እነርሱን ለመጥራት እምቢልታ ነፋ፤


ሩት ግን እንዲህ አለቻት፦ “ተለይቼሽ እንድመለስ አታስገድጅኝ! አንቺ ወደምትሄጂበት ሁሉ እሄዳለሁ፤ አንቺ በምትኖሪበት እኖራለሁ፤ ሕዝብሽ ሕዝቤ፥ አምላክሽም አምላኬ ይሆናል፤


ሳሙኤልም እግዚአብሔር ያዘዘውን ለማድረግ ወደ ቤተልሔም ሄደ፤ እዚያም እንደ ደረሰ የከተማይቱ መሪዎች በፍርሃት እየተንቀጠቀጡ ወደ ሳሙኤል ቀርበው “አመጣጥህ ለሰላም ነውን?” ሲሉ ጠየቁት።


እርሱም “አዎ! ለሰላም ነው፤ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀርብ ዘንድ መጥቻለሁ፤ ራሳችሁን በማንጻት ወደ እኔ ኑ” ሲል መለሰላቸው። እሴይና ልጆቹም ራሳቸውን እንዲያነጹ በመንገር ወደ መሥዋዕቱ እንዲመጡ ጠራቸው።


ሳኦልም ባለሟሎችን እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ የብንያም ሰዎች አድምጡኝ! በውኑ የእሴይ ልጅ ዳዊት ለሁላችሁም ለእያንዳንዳችሁ የእርሻ መሬትና የወይን ተክል ቦታ የሚሰጣችሁና በሠራዊቱም ውስጥ ሻለቆችና የመቶ አለቆች አድርጎ የሚሾማችሁ ይመስላችኋልን?


እንግዲህ ስሕተተኛው ማንኛችን እንደ ሆንን በመለየት እግዚአብሔር ፍርዱን ይስጥ! እኔ በአንተ ላይ ምንም ዐይነት ጒዳት ላደርስብህ ስለማልፈልግ በእኔ ላይ ስለምታደርገው ክፉ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ራሱ ይበቀል።


‘ክፉ ነገርን የሚያደርጉ ክፉ ሰዎች ብቻ ናቸው’ የተባለውን ጥንታዊ አነጋገር ታውቃለህ፤ ስለዚህም እኔ በአንተ ላይ ጒዳት ላደርስብህ አልፈልግም።


ዳዊትም ይህን ተናግሮ እንደ ጨረሰ ሳኦል “ልጄ ዳዊት ሆይ! በእውነት ይህ የአንተ ድምፅ ነውን?” ብሎ ማልቀስ ጀመረ፤


ከእነርሱም አንዳንዶቹን የሺህ አለቆችና የኀምሳ አለቆች አድርጎ ይሾማል፤ ወንዶቹ ልጆቻችሁ የንጉሡ ሁዳድ አራሾችና መከር ሰብሳቢዎች ይሆናሉ፤ ሌሎችም የጦር መሣሪያና የሠረገላ ዕቃ ሠራተኞች ይሆናሉ።


跟着我们:

广告


广告