Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘካርያስ 8:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ አባቶቻችሁ እጅግ ባስቈጡኝ ጊዜ ክፉ ለማድረግ እንዳሰብኩ፥ እንዳልተጸጸትኩም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “አባቶቻችሁ ባስቈጡኝ ጊዜ ያለ አንዳች ሐዘኔታ ጥፋት ላመጣባችሁ እንደ ወሰንሁ፣” ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 “እኔ የሠራዊት አምላክ ይህን ተናግሬአለሁ፤ የቀድሞ አባቶቻችሁ ባስቈጡኝ ጊዜ ባለመራራት ቅጣት ላመጣባችሁ ወሰንኩ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ አባቶቻችሁ እጅግ ባስቈጡኝ ጊዜ ክፉ ለማድረግ እንዳሰብሁ፥ እንዳልተጸጸትሁም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ አባቶቻችሁ እጅግ ባስቈጡኝ ጊዜ ክፉ ለማድረግ እንዳሰብሁ፥ እንዳልተጸጸትሁም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥

参见章节 复制




ዘካርያስ 8:14
12 交叉引用  

እነርሱ ግን የጌታ ቁጣ በሕዝቡ ላይ እስኪወርድባቸው ድረስ፥ ፈውስም እስከማይገኝላቸው ድረስ፥ በጌታ መልክተኞች ይሳለቁ፥ ቃላቱንም ያቃልሉ፥ በነቢያቱም ላይ ያፌዙ ነበር።


የጌታ ምክር ግን ለዘለዓለም ይኖራል፥ የልቡም አሳብ ለልጅ ልጅ ነው።


የሠራዊት ጌታ እንዲህ ብሎ ምሏል፦ “እንደ ተናገርሁ በእርግጥ ይሆናል፥ እንዳሰብሁም እንዲሁ ይቆማል።


ያም ሰው ጌታ ሳይጸጸት እንደ ገለበጣቸው ከተሞች ይሁን፥ በማለዳም ልቅሶን በቀትርም ጩኸትን ይስማ፤


ለእናንተ የማስበውን አሳብ እኔ ጠንቅቄ አውቃለሁ፥ ይላል ጌታ፤ ለወደፊት የሠመረ ጊዜና ተስፋ ልሰጣችሁ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።


እንዲህም ይሆናል፤ እነርሱን ልነቅላቸውና ልሰባብራቸው፥ ላፈርሳቸውና ላጠፋቸው፥ ክፉም ላደርግባቸው እንደ ተጋሁ፥ እንዲሁ ልሠራቸውና ልተክላቸው እተጋለሁ፥ ይላል ጌታ።


ጌታ እንዲህ ይላልና፦ ይህን እጅግ ክፉ ነገር ሁሉ በዚህ ሕዝብ ላይ እንዳመጣሁ፥ እንዲሁ ለእነርሱ የተናገርሁትን በጎነት ሁሉ አመጣላቸዋለሁ።


ስለዚህ ምድር ታለቅሳለች፥ በላይም ሰማይ ይጠቁራል፤ ተናግሬአለሁና፥ አስቤአለሁም፤ አልጸጸትም ከእርሱም አልመለስም።”


እኔ ጌታ ተናግሬአለሁ፤ ይፈፀማል፥ እኔም አደርገዋለሁ፤ አልቆጠብም፥ አልራራም፥ አልጸጸትም። እንደ መንገድሽና እንደ ሥራሽ ይፈርዱብሻል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ጌታ በአባቶቻችሁ ላይ እጅግ ተቈጥቶ ነበር።


ነገር ግን ለአገልጋዮቼ ለነቢያት ያዘዝኳቸው ቃሎቼና ሥርዓቴ በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሱምን? ከዚያ እነርሱም ተጸጽተው፦ “የሠራዊት ጌታ በመንገዳችንና በሥራችን መጠን ሊያደርግብን ያሰበውን እንዲሁ አድርጎብናል” በማለት ተቀበሉ።


跟着我们:

广告


广告