Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘካርያስ 14:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ጌታም ከኢየሩሳሌም ጋር የተዋጉትን አሕዛብ ሁሉ የሚቀሥፍበት ቸነፈር ይህ ነው፤ በእግራቸው ሲቆሙ ሥጋቸው ይበሰብሳል፥ ዐይኖቻቸውም በዓይነስባቸው ውስጥ ይበሰብሳል፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን የወጓትን አሕዛብ ሁሉ የሚመታበት መቅሠፍት ይህ ነው፤ ገና በእግራቸው ቆመው ሳሉ ሥጋቸው ይበሰብሳል፤ ዐይኖቻቸው በጕድጓዶቻቸው ውስጥ እንዳሉ ይበሰብሳሉ፤ ምላሶቻቸውም በአፎቻቸው ውስጥ እንዳሉ ይበሰብሳሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ኢየሩሳሌምን ለመውጋት በሚነሣሡ ሕዝቦች ላይ እግዚአብሔር ቀሣፊ በሽታ ያመጣባቸዋል፤ በሕይወት እያሉ ሥጋቸው ይበሰብሳል፤ ዐይናቸው በዐይነስባቸው ውስጥ፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እግዚአብሔርም ከኢየሩሳሌም ጋር የተዋጉትን አሕዛብ ሁሉ የሚቀሥፍበት ቸነፈር ይህ ነው፣ በእግራቸው ሲቆሙ ሥጋቸው ይበሰብሳል፥ ዓይኖቻቸውም በዓይነስባቸው ውስጥ ይበሰብሳሉ፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እግዚአብሔርም ከኢየሩሳሌም ጋር የተዋጉትን አሕዛብ ሁሉ የሚቀሥፍበት ቸነፈር ይህ ነው፥ በእግራቸው ሲቆሙ ሥጋቸው ይበሰብሳል፥ ዓይኖቻቸውም በዓይነስባቸው ውስጥ ይበሰብሳሉ፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል።

参见章节 复制




ዘካርያስ 14:12
34 交叉引用  

አንተም ከደዌው ጽናት የተነሣ አንጀትህ በየዕለቱ እስኪ ወጣ ድረስ በክፉ የአንጀት ደዌ ትያዛለህ።’ ”


የሰውነቱ ክፍሎች ይጠፋሉ፥ የሞትም የበኩር ልጅ ሰውነቱን ይበላል።


የቁጣህን ጽናት ማን ያውቃል? የቁጣህንስ ግርማ ማን ያውቃል?


እኔ ደግሞ እንዲህ አደርግባችኋለሁ፤ ፍርሃትን፥ ነፍስን የሚያኮስስና ዓይንን የሚያፈዝዝ ክሳትና ትኩሳት አመጣባችኋለሁ፤ ጠላቶቻችሁም ይበሉታልና ዘራችሁን በከንቱ ትዘራላችሁ።


እነዚህም ነገሮች ተደርገውባችሁ እንኳ ባትሰሙኝ፥ ስለ ኃጢአታችሁ ሰባት እጥፍ ጨምሬ ዳግመኛ እቀጣችኋለሁ።


“እኔንም በመቃወም ብትሄዱ ልትሰሙኝም ባትፈልጉ፥ እንደ ኃጢአታችሁ መጠን ሰባት እጥፍ ቸነፈር እጨምርባችኋለሁ።


እኔም ደግሞ እናንተን በመቃወም እሄዳለሁ፤ እኔም ስለ ኃጢአታችሁ ሰባት እጥፍ እመታችኋለሁ።


እኔ ደግሞ በቁጣ እናንተን በመቃወም እሄዳለሁ፤ እኔም ስለ ኃጢአታችሁ ሰባት እጥፍ እቀጣችኋለሁ።


እኔ ብዙም ሳልቆጣቸው እነርሱ ክፋትን ስላገዙት፥ በምቾት በሚኖሩት አሕዛብ ላይ እጅግ ተቈጥቻለሁ።


በዚያም ቀን በኢየሩሳሌም ላይ የሚነሡትን አሕዛብ ሁሉ ለማጥፋት እፈልጋለሁ።


በፈረሶች፥ በበቅሎዎች፥ በግመሎች፥ በአህዮች፥ እንዲሁም በዚያም ሰፈር ባሉ እንስሶች ሁሉ ላይ በሰዎች ላይ እንደ ሆነው ዓይነት ቸነፈር በእነርሱም ላይ ይሆናል።


የግብጽም ወገን ባይወጣ ወደዚያም ባይሄድ፥ ጌታ የዳስ በዓልን ለማክበር የማይወጡትን አሕዛብ የሚቀሥፍበት ቸነፈር በእርሱ ላይ ይመጣል።


ጌታም ይወጣል፥ በጦርነትም ቀን እንደሚዋጋ ከእነዚያ አሕዛቦች ጋር ይዋጋል።


እኔም፦ “እነዚህ የመጡት ምን ሊሠሩ ነው?” አልኩት። እርሱም፦ “አንድ ሰው ራሱን ቀና ማድረግ እስኪሳነው ድረስ እነዚህ ቀንዶች ይሁዳን የበተኑ ናቸው፤ እነዚህ ግን ሊያስፈራሯቸው፥ የይሁዳንም አገር ለመበተን ቀንዳቸውን ያነሡትን የአሕዛብን ቀንዶች ሊቆርጡ መጥተዋል” ብሎ ተናገረ።


ለእግዚአብሔርም ክብር ስላልሰጠ ያንጊዜ የጌታ መልአክ መታው፤ በትልም ተበልቶ ሞተ።


ጌታ ልትወርሳት ከምትገባባት ምድር ላይ እስኪያጠፋህ ድረስም ቀሣፊ በሽታ ይልክብሃል።


ጌታ እስክትጠፋ ድረስ በሚቀሥፍ በሽታ ንዳድና ዕባጭ፥ ኀይለኛ ሙቀትና ድርቅ፥ ዋግና አረማሞ ይመታሃል።


ጌታ አስፈሪ መቅሠፍት፥ አስጨንቆህ የሚቆይ መዓት መቅሠፍት፥ አሠቃቂና ጽኑ በሽታ በአንተና በዘሮችህ ላይ ይልክባችኋል።


ያየሃቸውም ዐሥር ቀንዶችና አውሬው አመንዝራይቱን ይጠላሉ፤ ይበዘብዟታል፥ ራቁትዋንም ያደርጓታል፤ ሥጋዋንም ይበላሉ፤ በእሳትም ያቃጥሉአታል።


跟着我们:

广告


广告