本书并非出自上帝启示,且不属于基督教正典或犹太教塔纳赫的一部分。仅为历史与研究目的而展示。 查看完整说明 መጽሐፈ ጦቢት 6:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 ጋኔኑ ጭሱ ሲሸተው ሽሽቶ ይሄዳል ወደ እርሷም ከቶ ተመልሶ አይመጣም። አብራችሁ ከመተኛታችሁ በፊት ሁለታችሁም ለመጸለይ ተነሱ፥ የሰማዩ ጌታ ጸጋውንና ከለላውን እንዲሰጣችሁ ለምኑት። አትፍራ! ከጥንት ጀምሮ እርሷ የተወሰነችው ለአንተ ነው፥ የምታድናትም አንተ ነህ። ቃሌን እሰጥሃለሁ እርሷ አንተን ትከተላለች፥ እንደ ወንድሞች የሚሆኑልህ ልጆችንም ትወልድልሃለች፥ አትጨነቅ።” ጦቢያ የሩፋኤልን ንግግር ባደመጠ ጊዜና እርሷ ከዘሩና ከአባቱ ወገን የሆነች እኀቱ መሆንዋን ባወቀ ጊዜ በጣም ወደዳት፥ ልቡም ከእርሷ ጋር ሆነ። 参见章节 |