ማሕልየ መሓልይ 5:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 አንቺ በሴቶች ዘንድ የተዋብሽ ሆይ፥ ከሌላ ወዳጅ ይልቅ ፍቅረኛሽ ምን አለው? ይህን የሚያህል የምታስምይን? ከሌላ ወዳጅ ይልቅ ፍቅረኛሽ ምን አለው? 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም9 አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተዋብሽ ሆይ፤ ውድሽ ከሌሎች እንዴት ቢበልጥ ነው? እስከዚህ የምትማጠኚንስ፣ ውድሽ ከሌሎች እንዴት ቢበልጥ ነው? 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተዋብሽ ሆይ! በውኑ የአንቺ ፍቅረኛ ከሌሎች የተለየ ነውን? ስለ እርሱ ይህን ያኽል ዐደራ የምትዪን? እርሱ ከሌሎች የሚለይበት ነገር ምንድን ነው? 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 አንቺ በሴቶች ዘንድ የተዋብሽ ሆይ፥ ከወንድሞች ልጆች ይልቅ ልጅ ወንድምሽ ማን ነው? ይህን ያህል መሐላ አምለሽናልና ከወንድሞች ልጆች ይልቅ ልጅ ወንድምሽ ማን ነው? 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 አንቺ በሴቶች ዘንድ የተዋብሽ ሆይ፥ ከሌላ ወዳጅ ይልቅ ውድሽ ማን ነው? ይህን የሚያህል አምለሽናልና ከሌላ ወዳጅ ይልቅ ውድሽ ማን ነው? 参见章节 |